AMN- መስከረም 27/2017 ዓ.ም
ጉዳዩን አስመልክቶ ኤ ኤም ኤን ያነጋገራቸው ሰመራ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምድር መምህር ኖራ ያኒሞዖ ባለፉት ሶስት ሳምንታት በሬክተር ስኬል ከ4 ነጥብ 5 እስከ ትናንት ምሽት ደግሞ 4 ነጥብ 9 የተመዘገበ የመሬት መንቀጥቀጥ በተለያዩ አጋጣሚዎች በአካባቢው መከሰቱን ገልጸዋል፡፡
ትናንት መስከረም 26 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት 2፡10 ገደማ የተከሰተው የመሬት መንቀጥቀጥም በንብረትና በእንስሳት ላይ መጠነኛ ጉዳት ማድረሱንም ለኤ ኤም ኤን ተናግረዋል፡፡
አደጋው በተከሰተበት ሳቡሬ ቀበሌ መረጃ የመሰብሰብ ስራ እየተከናወነ መሆኑን ያስታወቀው ዩኒቨርሲቲው ነዋሪዎች ከፈንታሌ ኮረብታማ ቦታ እና ከከሰም ግድብ ርቀው እንዲቆዩ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራ እያከናወነ መሆኑንም ምሁሩ ገለጸዋል፡፡
የመሬት መንቀጥቀጡ በመሬት ውስጥ አልፎ አዲስ አበባ ውስጥ ልዩ ልዩ ቦታዎች ንዝረቱ መሰማቱን ገልጸው አደጋው እዚህ አዲስ አበባ የተከሰተ ሳይሆን ንዝረቱ በመሬት ውስጥ ተጉዞ መጥቶ በመዲናዋ ያሉ ህንጻዎችን ማንቀጥቀጡን ተናግረዋል።
ዩኒቨርሲቲው የመሬት መንቀጥቀጡን ተጨማሪ መረጃ ለማጣራት እየሰራ መሆኑንም ነው ምሁሩ የገለጹት ፡፡
በሄለን ጀምበሬ