AMN – ታኀሣሥ 28/2017 ዓ.ም
ጤና ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጋር በመሆን የመሬት መንቀጥቀጡ በጤና ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ እና መደረግ ያለበትን ጥንቃቄ ለመለየትና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት እንዲያስችል ጥናት ለማድረግ የተለያየ የሙያ ስብጥር ያላቸው የባለሙያዎች ቡድን ወደ ቦታው መላኩን አስታውቋል፡፡
በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ከጤና ጋር በተገናኘ በቀጣይ ምን ሊከሰት እንደሚችል ፣ ምን አይነት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግና መወሰድ ባለባቸው እርምጃዎች ዙሪያ ጥናት ለማድረግ ከተለያዩ የጤና ሙያ ዘርፎች የተውጣጣ ቡድን በቦታው መድረሱን ከሚኒስቴሩ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡
ከክልሉ ጤና ቢሮ እና ከህብረተሰብ ጤና ኢንስቲቱት ጋር በመሆን አስፈላጊዉን ፈጣን ምላሽ በመስጠት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑም ተመላክቷል።