በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል የተደረሰው የአንካራ ሥምምነት የሁለቱን እህትማማች ሀገሮች ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ የሚደነቅ ነው-ኢጋድ

You are currently viewing በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል የተደረሰው የአንካራ ሥምምነት የሁለቱን እህትማማች ሀገሮች ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ የሚደነቅ ነው-ኢጋድ

AMN – ታኀሣሥ 3/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያና በሶማሊያ መካከል የተደረሰው የአንካራ ሥምምነት የሁለቱን እህትማማች ሀገሮች ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር በመሆኑ የሚደነቅ ነው ሲል የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግሥታት (ኢጋድ) አስታወቀ፡፡

የኢጋድ ዋና ፀሃፊ ወርቅነህ ገበየሁ (ዶ/ር) ሥምምነቱን በተመለከተ በሰጡት መግለጫ፣ የምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነመንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መንግስት መካከል የተደረሰውን ስምምነት እንደሚደግፍ ገልጸዋል፡፡

ሥምምነቱ በሁለቱ እህትማማች አገሮች መካከል የቆየውን ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር እንደሚረዳም ጠቁመዋል፡፡

እንዲሁም ስምምነቱ የሁለትዮሽ ጉዳዮችን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የገለጹት ዋና ፀሃፊው በአፍሪካ ቀንድ የጋራ ችግሮችን ለመፍታት እና ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ዲፕሎማሲያዊ ጥረቶች አስፈላጊ መሆናቸውን አንስተዋል፡፡

ስምምነቱ እንዲደረስ ያደረጉትን የሁለቱን ሀገራት መሪዎች እና የሁለቱ ሀገራት መሪዎችን እንዲወያዩ በማድረግ ከፍተኛ ጥረት ላደረጉት የቱርኩ ፕሬዚዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶኻን ዋና ፀሃፊው ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የኢጋድ አባል ሀገራት የሆኑት ኢትዮጵያና ሶማሊያ የደረሱት ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ኢጋድ ድጋፍ ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review