በኢትዮጵያ እና በአዘርባጃን መካከል ያለው የሁለትዮሽ ትብብር እና ግንኙነት እያደገ መጥቷል-አቶ ተስፋዬ ዳባ

You are currently viewing በኢትዮጵያ እና በአዘርባጃን መካከል ያለው የሁለትዮሽ ትብብር እና ግንኙነት እያደገ መጥቷል-አቶ ተስፋዬ ዳባ

AMN-መስከረም 20/2017 ዓ.ም

ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ፍትሕ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተስፋዬ ዳባ የተመራ የልዑክ ቡድን ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ካሚራን አሊዬቭ ጋር ተወያይቷል።

ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጽያ እና በአዘርባጃን መካከል ያለው የሁለትዮሽ ትብብር እና ግንኙነት በጥሩ ሂደት እያደገ መምጣቱንና ይህም ጠቀሜታው የጎላ መሆኑነ ገልጸዋል፡፡

በሁለቱ ሀገራት የሚኖረው የሁለትዮሽ የሕግና የፍትሕ ሥርዓት ግንባታ በሕግ ማዕቀፍ መታሠር እንዳለበትም ተናግረዋል።

ለዚህም የሁለትዮሽ ስምምነቱ ከሁለቱ ሀገራት በጋራ በተወጣጣ የስራ ቡድን ተዘጋጅቶ በመጪው ጥር 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ እንዲፈራረሙ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕጉ ግብዣ አቅርበዋል።

የአዘርባጃን ሪፐብሊክ ዋና ጠቅላይ አቃቤ ህግ ካሚራን አሊዬቭ በበኩላቸው፣ ከኢትዮጵያ ጋር በህዝባዊ ንቅናቄ ማዕቀፍ ውስጥ ያለው ትብብር ከፍተኛ ደረጃ ላይ መድረሱን እና ትብብሩም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተጠናከረ መምጣቱን ገልጸዋል።

ህዳር 15 በባኩ ከአዘርባጃን ሪፐብሊክ ጠቅላይ አቃቤ ህግ ጋር በመተባበር በሚደረገው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአደንዛዥ ዕፅ እና ወንጀል ፅህፈት ቤት ጋር በጋራ በሚዘጋጀዉ ጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ላይ አቶ ተስፋዬ ዳባ እንዲሳተፉ ግብዣ አቅርበውላቸዋል።

የልዑክ ቡድኑ በምክትል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ቢሮ ውስጥ ያለውን የምርመራ ቢሮዎች እና በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዋና መስሪያ ቤት ያለውን ሙዚዬም የጎበኘ ሲሆን በቀጣይም የአንድ ማዕከል አገልግሎት ልምድ ልውውጥ እና ጉብኝት እንደሚደረግ ከፍትህ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review