በኢትዮጵያ እና ፓኪስታን መካከል ያለውን ፓርላሜንታዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ይሰራል:- ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)

You are currently viewing በኢትዮጵያ እና ፓኪስታን መካከል ያለውን ፓርላሜንታዊ ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር ይሰራል:- ዲማ ኖጎ (ዶ/ር)

AMN – ጥር 14/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ እና ፓኪስታን መካከል ያለውን ፓርላሜንታዊ ግንኙነት እና የህዝብ ለህዝብ ግንኝነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ኖጎ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ሰብሳቢው ይህንን ያሉት በኢትዮጵያ የፓኪስታን አምባሳደር አቲፍ ሻሪፍ ሚያን ተቀብለው ባነጋጉረበት ወቅት ነው፡፡

ሁለቱ ሀገራት በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ እና በማህበራዊ ዘርፍ የቆየ ግንኙነት አለቸው ያሉት ዶ/ር ዲማ ፤ ይህንንም ግንኙነት የበለጠ ለማጠናከር እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

በአፍሪካ ሰላም እና ደህንነትን ለማረገገጥ ኢትዮጵያ እየተጫወተችው ያለው ሚና ከፍተኛ ነው ያሉ ሲሆን፤ በቀጣይም በተለያዩ የአፍሪካ ክፍሎች ጸረ-ሰላም ሀይሎችን ለመከላከል በሚደረገው ጥረት ከአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት ጋር በጋራ እንደምትሰራ ተናግረዋል፡፡

የፓኪስተን አምባሳደር አቲፍ ሻሪፍ ሚያን በበኩላቸው፤ የሁለቱን ሀገራት ፓርላሜንታዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል የሁለቱ ሀገራት የፓርላማ ወዳጅነት ቡድን አባላት የእርስ በእርስ የልምድ ልውውጥ የሚያደርጉበት መድረክ እንደሚፈጠር ጠቁመዋል፡፡

ሁለቱ ሀገራት በተለያዩ የአለም መድረኮች ላይ ብሄራዊ ጥቅሞቻቸውን እና ፍላጎቶቻቸውን ለማስጠበቅ በጋራ እንደሚሰሩም አምባሳደሩ ገልጸዋል፡፡

በምክር ቤቱ የውጭ ግንኙነት እና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ ፈትሂ ማህዲ (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት በኢኮኖሚው ዘርፍ የተለየዩ ማሻሻያዎችን በማድረግ በዘርፉ የነበሩ ችግሮችን ለመፍታት እየሰራች ነው ብለዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ በህዝብ ቁጥር ብዛት በአፍሪካ ሁለተኛ ሀገር ናት ያሉት ምክትል ሰብሳቢው፤ ከዚህም አንፃር ከጎረቤት ሀገራት የባህር በር ለማግኘት በሰላማዊ እና ሰጥቶ በመቀበል መርህ እየሰራች እንደሆነ መናገራቸውን ከምክር ቤቱ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review