የሆሳዕና በዓል በኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ልደታ ማሪያም ካቶሊክ ካቴድራል በድምቀት እየተከበረ ይገኛል።
በበዓሉም የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ ካርዲናል ብርሀነኢየሱስ ሱራፌል፣ የሀይማኖት አባቶችና የእምነቱ ተከታዮች ተገኝተዋል።
ዕለቱ የዐቢይ ጾም የመጨረሻው ሳምንት እሁድ ላይ የሚውል ሲሆን ይህን ዕለት የኢትዮጵያ ካቶሊክ እምነት ተከታዮች በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ያከብሩታል።
በዓሉ በፀሎት፣ በዝማሬ፣ በምስጋና እና በሌሎች ሀይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ይገኛል።
በአሸናፊ በላይ



See insights and ads
All reactions:
1212