በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከተማ አቻ ሲለያዩ ወላይታ ድቻ አሸነፈ

You are currently viewing በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከተማ አቻ ሲለያዩ ወላይታ ድቻ አሸነፈ

AMN – የካቲት 27/2017 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ከባህርዳር ከተማ አቻ ሲለያዩ ወላይታ ድቻ አሸንፏል፡፡

የ21ኛ ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬም ሲቀጥል ከባህርዳር ከተማ ጋር ጨዋታውን ያደረገው ፋሲል ከነማ 0ለ0 በሆነ አቻ ውጤት አጠናቋል።

ከቀኑ ዘጠኝ ሰዓት ጀምሮ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስታዲየም በተደረገው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ተመጣጣኝ ፋክክር ቢደረግበትም ግብ ሳይቆጠርበት በአቻ ውጤት ተጠናቋል።

ፋሲል ከነማዎች በ58ኛው ደቂቃ ላይ የፍጹም ቅጣት ምት ቢያገኙም አዲሱ ፈራሚ ቢኒያም ጌታቸው ሳይጠቀምበት ቀርቷል።

አፄዎቹ ያለፉትን 3 ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም፤ በሁለቱ ሲሸነፉ በአንዱ አቻ ተለያይተዋል።

ምሽት 12 ሰዓት ላይ የተጀመረው የቅዱስጊዮርጊስና የወላይታ ድቻ ጨዋታ በወላይታ ድቻ 1ለ0 አሸናፊነት ተጠናቋል።

አብነት ደምሴ የወላይታ ድቻን የማሸነፊያ ብቸኛ ግብ አስቆጥሯል ።

የጦና ንቦቹ ማሸነፋቸውን ተከትሎ ነጥባቸውን ወደ 30 በማሳደግ 6ኛ ደረጃ ሲቀመጡ ሶስተኛ ተከታታይ ሽንፈት ያስተናገዱት ፈረሰኞቹ በ29 ነጥብ 7ኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

ሊጉ ነገም ሲቀጥል በ21ኛ ሳምንት የመጨረሻ ቀን ጨዋታ መቻል ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርስቲና ኢትዮጵያ መድን ከድሬደዋ ከተማ ይጫወታሉ።

በሀና ታሪኩ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review