በከተማዋ ለተመዘገበው እመርታዊ ለውጥ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ድርሻ ትልቅ ነው- አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

You are currently viewing በከተማዋ ለተመዘገበው እመርታዊ ለውጥ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ድርሻ ትልቅ ነው- አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

AMN – መጋቢት 6/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት በመንግስት ዋና ተጠሪ አስተባባሪነት በዛሬው ዕለት በተለያዩ ሀገራዊ አንድነትን በሚያጠናክሩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለምክር ቤቱ አባላት ተሰጥቷል።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ ምክርቤት አፈ ጉባኤ ወይዘሮ ቡዜና አልከድር፣ በከተማዋ ለተመዘገበው እምርታዊ ለውጥ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ድርሻ ትልቅ ነው ብለዋል፡፡

ለዚህ ውጤት መሰረቱ ደግሞ የአዲስ ምዕራፍ ምክር ቤት በተቋማዊ አደረጃጀት እና በአሰራር ለውጥ ላይ የተመሰረተ የሪፎርም ስራዎችን መስራት በመቻሉ እንደሆነ አንስተዋል፡፡

በተለይም የውስጥ አሰራር እና አደረጃጀቱ ላይ ልዩ ትኩረትና ርብርብ በማድረግ የምክርቤት አባላት ምክር ቤታዊ ተልዕኳቸውን በአቅምና በአስተሳሰብ መምራት የሚያስችል የአሰራርና አደረጃጀት መፍጠር ስለመቻሉ ተናግረዋል፡፡

የአሰራርና አባላት ስነ ምግባር ደንብን በማሻሻል፣ የምክር ቤት አባላትን ሚና በማሳደግ ትርጉም ያላቸው አደረጃጀቶች ማለትም የምክርቤት ጉዳዮች አማካሪ ኮሚቴ፣ የመራጭ ተመራጭ ትስስር አደረጃጀት፣ የመንግስት ተጠሪ እና የሴት ተመራጮች ኮከስ አብነታዊ ማሳያዎች እንደሆኑም አመላክተዋል፡፡

እነዚህ አደረጃጀቶች የምክር ቤት አባላት ያላቸውን ሙያ፣ አቅምና ልምድ በመጠቀም የምክር ቤት ተልዕኳቸውን በመወጣት በመራጩ ህዝብም ሆነ በአስፈፃሚ አካላት ያላቸውን ደረጃና ተቀባይነት በተግባር ማሳየት የተቻለበት እና እውቅናም የተስጠበት መሆኑን ማንሳታቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review