AMN – ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም
በከተማዋ በሰዉ ተኮር ስራዎች የተገኙ ዉጤቶችን አመራሩ በአገልግሎት አስጣጥ መድገም እንደሚገባዉ በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር(ዶ/ር) አሳሰቡ ፡፡
የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በየደረጃዉ ለሚገኙ አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል ::
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአዲስ አበባ ፐብሊክ ሰርቪስ እና የሰዉ ሀብት ልማት ቢሮ ኃላፊ ጀማሉ ጀንበር (ዶ/ር) ባለፉት ዓመታት ምቹ የስራ አካባቢ የመፍጠር እና አገልግሎቱን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸዉን ተናግረዋል ::
ህዝቡ ከሚፈልገዉ አገልግሎት አንፃር ብዙ መስራት እንደሚጠበቅ የተናገሩት ሃላፊዉ ህብረተሰቡን በተቀመጠዉ መስፈርት መሰረት ማገልገል ይገባል ብለዋል ::
በከተማዋ በሰዉ ተኮር ስራዎች የተገኙ ዉጤቶችን በአገልግሎት አስጣጥ መድገም እንደሚገባም አሳስበዋል ::
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል አመራሩ የተጣለበትን ኃላፊነት ተረድቶ ህብረተሰቡን በቅንነት እና በታማኝነት ማገልገል ይገባልዋ ብለዋል ::
በቴዎድሮስ ይሳ