በከተማዋ እየተፈጠረ ያለው የስራ እድል ፤ ክህሎት መር የስራ እድል እንዲሆን እየተደረገ ነው፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

You are currently viewing በከተማዋ እየተፈጠረ ያለው የስራ እድል ፤ ክህሎት መር የስራ እድል እንዲሆን እየተደረገ ነው፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN – የካቲት 12/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የ2017 ዓ.ም 4ኛ የስራ ዘመን 2ኛ መደበኛ ጉባኤውን ያካሄደ ይገኛል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የአስተዳደሩን የ6 ወራት እቅድ አፈፃፀም ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡

ከንቲባዋ ባቀረቡት ሪፖርትም በከተማዋ እየተፈጠረ ያለው የስራ ዕድል ክህሎት መር ሆኖ እንዲመራ እየተደረገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ባለፋት ስድስት ወራት ውስጥ ለ142 ሺህ 908 ነዋሪዎች ቋሚ የስራ ዕድል መፍጠር ተችሏል።

ከዚህም ውስጥ 68 በመቶ የተፈጠረው የስራ እድል በአገልግሎት ዘርፍ ሲሆን በኢንዱስትሪ ዘርፍ ደግሞ 21 በመቶ እንዲሁም ቀሪው በከተማ ግብርና ዘርፍ የተፈጠረ የስራ እድል መሆኑንም አመልክተዋል።

ከተፈጠረው አጠቃላይ የስራ እድል ውስጥ 53.3 በመቶው ለሴቶች የተፈጠረ የስራ እድል መሆኑን ከንቲባዋ ጠቁመዋል ፡፡

የኢንዱስትሪ ልማት ዘርፉን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ የአምራች ኢንዱሰትሪዎችን አቅም የማጎልበትና የሚያነሱትን የመሰረተ ልማት ጥያቄዎችን የመፍታት ስራ ተከናውኗል።

የመብራት ፣ የውሀ የመንገድ ችግር የነበረባቸውን ኢንዱስትሪዎች በመለየት 231 ኢንዱስትሪዎች የመብራት ችግራቸው መፈታቱ ተመልክቷል፡፡

ለ276 ኢንዱስትሪዎች የካፒታል ሊዝ መቅረቡን ፣ 184 ኢንዱስትሪዎች ምርታቸውን ወደ ውጪ እየላኩ መሆኑም ተጠቁሟል ፡፡

1 ሺህ 671 አምራች ኢንዱስትሪዎች 725 ሚሊየን 480 ሺህ 810 ቶን ተኪ ምርት በማምረት 490 ሚሊየን 630 ሺህ 180 ዶላር የውጪ ምንዛሪ ማዳን መቻሉንም ነው ከንቲባዋ በሪፖርታቸው ያመለከቱት።

በሽመልስ ታደሰ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review