በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ የማሌዢያ ከተሞችን እየጎበኘ ነው

You are currently viewing በከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ የማሌዢያ ከተሞችን እየጎበኘ ነው

AMN- ጥቅምት 24/2017 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የተመራ የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ የማሌዢያ የተለያዩ ከተሞችን በመጎብኘት ላይ ነው፡፡

ጉብኝቱ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ማሌዢያ ጉብኝትን ተከትሎ ከፍተኛ እና ፈጣን የልማት ለውጥ ያስመዘገበችዉ ማሌዢያ የተከተለችዉ የትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂ ከአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን ለዉጥ ጋር ሲነፃፀር የልምድ ልውውጥ ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ ነዉ ተብሏል።

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች ልኡክ በትናትናው እለት ኳላላምፑር፣ ሳይበርጃን እና ሳንዌይ ከተሞችን የጐበኘ ሲሆን በዛሬው እለት ደግሞ የገንቲንግ የቱሪስት መዳረሻን በመጐብኘት ላይ እንደሚገኝ ከከንቲባ ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review