በኬንያ የሚኖሩ የዲያስፖራ አባላት ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ8 ሺህ ዶላር በላይ ቦንድ ገዙ

AMN ሀምሌ 27/2016

በኬንያ የሚኖሩ የቡርጂ ማህበረሰብ የዳያስፖራ አባላት በመጠናቀቅ ላይ ላለው ታላቁ ህዳሴ ግድብ የ8,050 ዶላር ወይም ከ644ሺ ብር በላይ ቦንድ ግዢ አካሄዱ።

የዳያስፖራ አባላቱ ናይሮቢ በሚገኘው የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሚሲዮን በመገኘት ነው የቦንድ ግዥውን ያከናወኑት።

አባላቱ በዕለቱ በተናጠል ከ100 እስከ 1,000 የአሜሪካ ዶላር ቦንድ የገዙ ሲሆን፣ የግድቡ ግንባታ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እያደረጉ እንዳሉም ይታወቃል።

በኬንያ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ባጫ ደበሌ ለዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላቱ ምስጋናቸውን አቅርበው ላሳዩት ከፍተኛ የሀገር ፍቅርና ተነሳሽነት አድናቆታቸውን ገልፀዋል።

በኬንያ የሚኖሩ የቡርጂ ማህበረሰብ የዳያስፖራ አባላት በተለያዩ ጊዜያት በሚደረጉ አገራዊ ጥሪዎች ላይ በንቃት የሚሳተፉ ሲሆን፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን የቦንድ ግዢ ላይ በከፍተኛ ንቃት ሲሳተፉ እንደነበር ከህዳሴ ግድብ ህዝባዊ ተሳትፎ ማስተባባሪያ ፅህፈት ቤት የተገኘው መረጃ ያሳያል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review