አዲስ ሚዲያ ኔትዎርከ( ኤ ኤም ኤን )መስከረም 7/2016 ዓ.ም
በመዲናዋ ህጋዊ ቀረጥ ሳይከፈልባቸው በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ 1ሺህ 812 ቴክኖ ሞባይል ስልኮች መርካቶ ከተራገፉ በኋላ ተይዘዋል፡፡
የአዲስ አበባ ፖሊስ ከህብረተሰቡ በደረሰው ጥቆማ መሰረት ባከናወነው ተግባር ዛሬ ንጋት ላይ በመዲናዋ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ልዩ ቦታው አዲስ አበባ የገበያ ማዕከል አካባቢ ሞባይል ስልኮቹ በ6 ካርቶን ታሽገው ከመኪና እንደተራገፉ መያዛቸው ተገልጿል፡፡
በወንጀሉ ላይ ተሳትፎ አለው የተባለ አንድ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ ምርመራ እየተጣራ እንደሚገን ከአዲስ አበባ ፖሊስ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ