AMN- ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ የ7 ሰዎች ሕይዎት አለፈ።
በወረዳው ላሾ እና 01 ቀበሌዎች የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ ከሟቾች በተጨማሪ በሁለት ሰዎች እና በንብረት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጿል።
በዞኑ የካዎ ኮይሻ ወረዳ ዋና አስተዳደሪ አቶ አበባየሁ ዮሐንስ የስጋት ቀጠናዎች ላይ አሁንም ሕብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ማስገንዘባቸውን የዞኑ ኮሙኒኬሽን ጽ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመለክታል።