AMN – ታኅሣሥ 28/2017 ዓ.ም
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ለእየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
ከንቲባዋ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፣ እየሱስ ክርስቶስ በሰው ልጆች እና በአምላክ መካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ በምህረት፣ በይቅርታ እና በታላቅ ፍቅር ወደ ምድር መምጣቱ ሰላምን እና ፍቅርን ለምድር እንዲሁም አብሮነት እንዲጎለብት ምሳሌ ለመሆን ነው ብለዋል::
ስለዚህ በዓሉን ስናከብር የእየሱስ ክርስቶስን ምሳሌነትን በመከተል የሰላም እሴቶችን እየገነባን፣ ፍቅራችንን ይበልጥ እያጎለበትን እንዲሁም አብሮነታችንን እያጠናከርን ሊሆን ይገባል ሲሉም አስፍረዋል::
በዓሉን ስናከብር ያላቸው ለሌላቸው ማዕድ በማጋራት ፍቅር፣ መተሳሰብና አብሮነት በሚገለጽበት መልክ እንዲሆን ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ከንቲባዋ በዓሉ የሰላም እና የደስታ በዓል እንዲሆንም ተመኝተዋል፡፡