በዓሉን ስናከብር ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን እያሰብን፣ የታረዙትን እያለበስን፣ የተራቡትን እያበላን፣ የተጠሙትን እያጠጣን ፍጹም ሰብዓዊነትን በተላበሰ ኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና ሊሆን ይገባል ሲሉ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኃላፊና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንት አደም ፋራህ መልዕክት አስተላለፉ።
አቶ አደም ፋራህ፣ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ለፋሲካ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በመልዕክታቸውም፣ በዓሉን ስናከብር ድጋፍ የሚሹ የህብረተሰብ ክፍሎችን እያሰብን፣ የታረዙትን እያለበስን፣ የተራቡትን እያበላን፣ የተጠሙትን እያጠጣን ፍጹም ሰብዓዊነትን በተላበሰ ኢትዮጵያዊ ስነ ልቦና ሊሆን እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
በተለይም የፓርቲያችን አመራር፣ አባላት እና ደጋፊዎች በዓሉ በፓርቲያችን የሰው ተኮርነት እና የሰብዓዊነት መርሆች ደምቆ እንዲከበር እያደረጋችሁ የምትገኙትን እንቅስቃሴ አጠናክራችሁ እንድትቀጥሉ እየጠየቅኩ በድጋሚ ፍቅር፣ ደስታን እና ሰላምን በጋራ የምንቋደስበት መልካም የፋሲካ በዓል እንዲሆን እመኛለሁ ብለዋል፡፡