AMN- መስከረም 28/2017 ዓ.ም
በያዝነው የምርት ዘመን የፍራፍሬ እና አትክልት ምርት በተለየ ሁኔታ አጥጋቢ ሆኗል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ የትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልእክት በብዙ የሀገራችን ክፍል እንደሚታየው የደቡብ ክልል በተፈጥሮ ሀብት የበለፀገ ነው ሲሉ አመልክተዋል።
34 ነጥብ 5 ሚሊዮን ኩንታል ፍራፍሬ እና 7 ነጥብ 6 ኩንታል አትክልት ተመርቷል ብለዋል።

ይኽን በደቡብ ክልል የታየ ስኬት በሌሎች ክልሎችም ለማስፋፋት የጋራ እድገት ለማስገኘት እና የምግብ ዋስትና ትልማችንን አሳክቶ ዘላቂ ልማትን በሚያረጋግጥ መልክ ጠንክረን መስራት ይገባል ሲሉም አመልክተዋል።