በደርባን የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ለ’ጽዱ ኢትዮጵያ’ ፕሮጀክት ከ410ሺ የደቡብ አፍሪካ ራንድ በላይ ድጋፍ አደረጉ

You are currently viewing በደርባን የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ለ’ጽዱ ኢትዮጵያ’ ፕሮጀክት ከ410ሺ የደቡብ አፍሪካ ራንድ በላይ ድጋፍ አደረጉ

AMN- ሰኔ 17/2016 ዓ.ም

በደቡብ አፍሪካ ኩዋዙሉናታል ክልል ደርባንና አካባቢው የሚኖሩ ዳያስፖራዎች በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ የቀረበውን ‘ጽዱ ኢትዮጵያ’ ንቅናቄን በመቀላቀል ከ410ሺ የደቡብ አፍሪካ ራንድ ወይም ከ1.3 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አደረጉ፡፡

በመርሀ ግብሩ ላይ በደቡብ አፍሪካ የኢፌዴሪ ልዩ መልዕክተኛና ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደር ሙክታር ከድር (ዶ/ር) የንቅናቄውን ፋይዳ በማስመልከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

በደርባንና አካባቢው የሚኖሩ እንዲሁም በመላው ደቡብ አፍሪካና ኤምባሲው በሚሸፍናቸው ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የሚኖሩ የኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ከሀገራቸው ጋር ያላቸው ትስስርና በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ያላቸው ተሳትፎም ጠንካራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በደርባንና አካባቢው የሚገኙ ኢትዮጵያውያን ለ’ጽዱ ኢትዮጵያ’ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ ላበረከቱት ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

የድጋፍ አስተባባሪ አባላትም ሀገር የሚገነባው በሀሉም ዜጎች ተጨባጭ ተሳትፎና ርብርብ መሆኑን በመገንዘብ በታላቅ ሀገራዊ ሞራልና ወኔ ላከናወኑት ስኬታማ የማስተባባር ሚና አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በመላው ደቡብ አፍሪካና በሌሎች ደቡባዊ አፍሪካ ሀገራት የሚኖሩ የዳያስፖራ አባላት ለ’ጽዱ ኢትዮጵያ’ ፕሮጀክት፣ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ የማጠናቀቂያ ምዕራፍ ግንባታና ለሌሎችም ለሀገራዊ የልማት ፕሮጀክቶች ድጋፍ በማድረግ ታሪካዊ አሻራቸውን የማሳረፍ ተግባራቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በወቅቱም በድጋፉ ለተሳተፉ የዳያስፖራ አባላትና የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላት የምስጋና እና የዕውቅና የምስክር ወረቀት በአምባሳደሩ ተበርክቶላቸዋል።

በመድረኩ ላይ የአስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን ጨምሮ በርካታ የዳያስፖራ አባላት የተገኙ ሲሆን፣ የኮሚቴ አባላቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ትስስር በማጠናከር በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ እያደረጉ ያለውን ሁለንተናዊ ተሳትፎ አጠናክረው እንደሚያስቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡

ለጽዱ ጎዳና – ኑሮ በጤና ሀገራዊ ፕሮጀክት ከዚህ ቀደም የሚሲዮኑ መሪዎች፣ መላው ሠራተኞችና የዳያስፖራ አባላት 5ሺ የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ማደረጋቸውን አስታውሶ የዘገበው ሚሲዮኑ ነው፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review