AMN-ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሲካሄድ የቆየው የማህበረሰብ ወኪሎች የአጀንዳ ልየታ የምክክር መድረክ ተጠናቋል።
የማህበረሰብ ወኪሎቹ ካለፈው ሰኞ ጥቅምት 18/2017 እስከ ዛሬ ጥቅምት 20/2017 ዓ.ም ድረስ ከወከሉት ማህበረሰብ ይዘዋቸው የመጡትን አጀንዳዎች በውይይት ሲያደራጁ ቆይተዋል፡፡
የማህበረሰብ ክፍል ወኪሎቹ በውይይት ያደራጁትን አጀንዳ በአደራ ተረክበው ከባለ ድርሻ አካላት ጋር የሚመካከሩ ወኪሎችንም መምረጣቸውን የኮሚሽኑ መረጃ ያሳያል፡፡
የክልሉ የባለድርሻ አካላት ምክክር ቀጥሎ ባሉ ቀናት የሚካሄድ መሆኑ ተመልክቷል፡፡
በዚህ መድረክ ከማህበረሰብ ወኪሎች የተመረጡ ተሳታፊዎችን ጨምሮ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች፣ የመንግስት አስፈፃሚ አካላት፣ የተፅዕኖ ፈጣሪ ግለሰቦች ወኪሎች እንዲሁም የሃይማኖት ተቋማትን ጨምሮ የልዩ ልዩ ማህበራትና ተቋማት ወኪሎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል፡፡