ሰሞኑን ሲካሄድ በነበረው የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ የዲሞክራቲክ ፓርቲ እጩ ሊ ጄ-ሚዮንግ አሸንፈዋል።
ጠቅላላ ከተሰጡ 95 በመቶ ድምፆች የዲሞክራቲክ ፓርቲው ሊ ጄ-ሚዮንግ 48.86 በመቶ በማግኘት 41.98 በመቶ ድምፅ ካገኙት ተፎካካሪያቸው የፒፕልስ ፓወር ፓርቲ እጩ ኪም ሙን-ሱ በመብለጥ ስልጣኑን ይዘዋል።
የቀድሞ ፕሬዝዳንት ዩን ሱክ-ዮል የስልጣን ዘመናቸው እስከ 2027 እ.ኤ.አ ድረስ የነበረ ቢሆንም ባለፈው ታህሳስ ወር ሃገሪቱ በወታደራዊ አስተዳደር እንድትተዳደር መወሰናቸውን ተከትሎ ከስልጣን በመባረር ክስ ተመስርቶባቸዋል።
ዩን ሱክ-ዮል ሃገሪቱ ለ6 ሰዓታት በወታደራዊ አስተዳደር ስር እንድትቆይ ካደረጓት በሗላ ላለፉት 6 ወራት ሃገሪቱ መረጋጋት ርቋት ቆይታለች።
አዲሱ ፕሬዝዳንት በሃሳብ የተከፋፈለች ሃገር፤ በአሜሪካ ታሪፍ የተጨነቁ ንግዶች እና ውሉ ያልታወቀ የዶናልድ ትራምፕ አጋርነት እንደሚጠብቃቸው ቢቢሲ ዘግቧል።
የምርጫው ውጤት ይፋ ከመደረጉ በፊት ሊ ሃገሪቱን አንድ የማድረግ ራዕይ እንዳላቸው ማስታወቃቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።
በሊያት ካሳሁን