AMN – መጋቢት 9/2017 ዓ.ም
በጀርመን የኢትዮጵያ አምባሳደር እስክንድር ይርጋ በጀርመን ከሚኖሩ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ማህበረሰብ አባላት ጋር በበይነ መረብ ውይይት አድርገዋል።
የኢትዮጵያ መንግስት በመጪዎቹ ዓመታት ውስጥ ተግባራዊ ለማድረግ ቅድሚያ በሚሰጣቸው በሀገራዊ የፖሊሲ ጉዳዮች፣ ውሳኔዎች እና አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደርጓል።
በውይይቱ ከተነሱ በዋና ዋና የፖሊሲ አቅጣጫዎች መካከልም ብሔራዊ ትርክት፣ የሀገር ግንባታ ስትራቴጂዎች፣ የሰላም ግንባታ እና ማጠናከር፣ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ አጀንዳዎች እንዲሁም የውጭ ፖሊሲ አቅጣጫዎች ይገኙበታል።
የዲያስፖራው ተሳታፊዎች በተቀመጡት የፖሊሲ አቅጣጫዎች አፈጻጸም ላይ ገንቢ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን ሰንዝረዋል።
ተለይተው የታወቁ የፖሊሲ ዓላማዎችን በተሳካ ሁኔታ ለማስፈጸምም በቅርበት ለመስራት እና ለመተባበር ስምምነት ላይ መደረሱን ከኤምባሲው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።