በግብርና ላይ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች የዘርፉን ማነቆዎች በተጨባጭ መፍታት ችለዋል

You are currently viewing በግብርና ላይ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች የዘርፉን ማነቆዎች በተጨባጭ መፍታት ችለዋል

AMN – ታኅሣሥ 20/2017 ዓ.ም

ባለፉት ስድስት አመታት በግብርና ላይ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች የዘርፉን ማነቆዎች በተጨባጭ መፍታት መቻላቸውን የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ገለጹ፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ(ዶ/ር) ግብርና በተለያዩ ስርዓቶች ውስጥ ትኩረት ተሰጥቶት ሲሰራበት መቆየቱን ገልጸዋል።

ይሁን እንጂ ከፖሊሲ ጀምሮ የተግባር እርምጃ ከመውሰድ አንጻር በቂ ትኩረት እንዳልተሰጠው ተናግረዋል።

የለውጡ መንግስት ዘርፉን ለማሻሻል ከወሰዳቸው ቀዳሚ እርምጃዎች ዋነኛው የፖሊሲ እርምጃ መሆኑን አስታውቀዋል።

በዚህም ለሜካናይዜሽንና ለመስኖ እርሻ የሚያገለግሉ መሳሪያዎችን ከቀረጥ ነጻ ወደ ሀገር በማስገባት በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ መቻሉን ነው ያስረዱት።

ይህም በዘርፉ የተከናወነ ትልቅ የፖሊሲ እርምጃ እንደሆነ ሚኒስትሩ አመላክተዋል።

አርሶ አደሮች ትራክተር እና ኮምባይነር ለማግኘት የፋይናንስ እጥረት እንደነበረባቸው ገልጸው አሁን ላይ እየሰሩ የሚከፍሉበት የባንክ አሰራር መዘርጋቱን ጠቁመዋል።

ይህም ለሜካናይዜሽን እርሻ መጎልበት መሰረታዊ ለውጥ መሆኑን ተከትሎ በርካቶችን የማሽነሪ ባለቤት አድርጓል።

በግብርና ላይ የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች የዘርፉን ማነቆዎች በተጨባጭ መፍታት ያስቻሉ መሆናቸውን ገልጸዋል።

ባለፉት ሶስት አመታት በተሰሩ ስራዎች በትራክተር የሚታረስ መሬት ምጣኔ 5 ሚሊዮን ሄክታር መድረሱን ጠቁመዋል።

የግብርና ሜካናይዜሽን ማሽነሪዎች በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች መታየት የቻሉበት እንደነበርም ጨምረው መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review