በጥንታዊቷ ሜክሲኮ አንድ የጠፋ ከተማ በአገሪቱ ጫካ ውስጥ ተገኘ

You are currently viewing በጥንታዊቷ ሜክሲኮ አንድ የጠፋ ከተማ በአገሪቱ ጫካ ውስጥ ተገኘ
  • Post category:ዓለም

AMN- ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም

ተመራማሪዎች በጥንታዊቷ ሜክሲኮ ጠፍቶ የነበረን ከተማ በአገሪቱ ጫካ ውስጥ በድንገት ማግኘታቸው ተሰምቷል፡፡

አርኪዮሎጂስቶች ባካሄዱት ቁፋሮ ፒራሚድ፣ የስፖርት ሜዳ፣ አምፊ ቴአትር እና ሰፈሮችን የሚያገናኙ መንዶችን የያዘውን ከተማ በደቡብ ምስራቅ ሜክሲኮ ካምፔች ማግኘታቸውን ገልጸዋል፡፡

የተመራማሪዎቹ ቡድን በከተማው ያገኟቸው ሶስት ትላልቅ ቦታዎች በመጠን የስኮትላንድ ዋና ከተማ ኤድንብራን ያክላል ብለዋል፡፡

ተመራማሪዎቹ ከተማውን ሊያገኙ የቻሉት በርቀት ሆኖ የሚሰራ ሊዳር በተሰኘ የጥናት ዘዴ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከተማው ከክርስቶስ ልደት በፊት (750-850) ከ30 እስከ 50ሺ የሚሆን ሰው ይኖርበት የነበረ ትልቅ ከተማ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል፡፡

ግኝቱ በወቅቱ በአካባቢው ምንም አይነት ሥልጣኔ አልነበረም የሚለውን የምእራቡን ዓለም አመለካከት እና እይታ የሚቀይር መሆኑን የምርምር ቡድኑ አባል የሆኑት ፕሮፌሰር ማርሴሎ ካኑቶ ተናግረዋል፡፡

ይልቁን ይሄው የዓለማችን ክፍል በርካታ እንቅስቃሴዎች የነበሩበት ና የባህል ሀብት ባለቤት ነውም ይላሉ ፕሮፌሰሩ፡፡

ከተማው በምን ምክንያት ሊጠፋ እንደቻለ እርግጠኛ መሆን ባይቻልም አርኪኦሎጂስቶቹ ግን የአየር ንብረት ለውጥ ዋንኛው መንስኤ እንደሚሆን ያስቀምጣሉ፡፡

16 ነጥብ 6 ስኩየር ኪሎ ሜትር ስፋት ያለው ከተማው ትላልቅ ህንጻዎች፣ ማያ የተሰኙ የአካባቢው ነዋሪዎች የአምልኮ እና የመቃብር ስፍራ የነበሩ ሁለት የፒራሚዶችን ያካተተ ነው፡፡

ከዚህም ሌላ ተመራማሪዎቹ አውልድ ቶማስና ፕሮፌሰር ካኑቶ በጫካው ውስጥ አገኘን ባሏቸው ሶስት ቦታዎች ላይ የተለያየ መጠን ያላቸውን በርካታ ህንጻዎች ማግኘታቸውን አብራርተዋል፡፡

በለንደን ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር የሆኑት ኤልሳቤጥ ግራሀም በበኩላቸው የማያ ሰዎች ከሌላው ዓለም በተገለለ መንደር ሳይሆን በሰለጠነ ከተሞች ውስጥ ይኖሩ እንደነበር ማሳያ ነው ይላሉ፡፡

የማያዎች ስልጣኔ ከክርስቶስ ልደት በፊት ከ800 ዓመት በኋላ እየከሰመ የመጠባትን ምክንያት የምርምር ውጤቱ አመልክቷል፡፡

ከህዝብ ብዛት የተነሳ እጅግ ተቀራርበው የሚኖሩ በመሆናቸው እና የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም አለመቻላቸው በከፊል በምክንያትነት አንስቷል፡፡

ጦርነትና በ16ኛው ክፍለ ዘመን ስፔናዊያን ተስፋፊዎች አካባቢው መውረራቸው ለማያ ከተማ መዳከምና መጥፋት ተጨማሪ ምክንያት እንደሚሆን ተጠቁሟል፡፡

ሊዳር ቴክኖሎጂን በመጠቀም በቀጣይም በርካታ የጠፉ ከተሞች ሊገኙ እንደምችሉ ፕሮፌሰር ካኑቶ ግምታቸውን አስቀምጠዋል፡፡ አርኪኦሎጂስቶች ገና ያላወቋቸው በርካታ ከተሞች ሊኖሩ እንደሚችሉ ማሳያ ነው መባሉን የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

በማሬ ቃጦ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review