በፍትህ ትራስፎርሜሽን የአዲስ አበባ ከተማ የተሞክሮ ማዕከል እንድትሆን መስራት ይገባል – አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

You are currently viewing በፍትህ ትራስፎርሜሽን የአዲስ አበባ ከተማ የተሞክሮ ማዕከል እንድትሆን መስራት ይገባል – አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

በፍትህ ትራስፎርሜሽን የአዲስ አበባ ከተማ የተሞክሮ ማዕከል እንድትሆን መስራት ይገባል – አፈ ጉባኤ ቡዜና አልከድር

AMN – ሚያዚያ 09/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የፍትህ ተቋማትን የሪፎርም ሂደት ገምግመዋል።

አፈ ጉባኤዋ በግምገማው ላይ እንደገለጹት፣ በፍትህ ትራስፎርሜሽን የአዲስ አበባ ከተማ የተሞክሮ ማዕከል እንድትሆን መስራት ይገባል ብለዋል።

በጥናት ብቻ ሳይሆን ህዝቡን እና ባለድርሻ አካላትን በማወያየት፣የሚነሱ ሀሳቦችንም እና አስተያየቶችን በግብዓትነት በመውሰድ የሪፎርሙ አካል ማድረግ እንደሚገባ ነው አፈጉባኤዋ የገለጹት፡፡

በተለይ ለአሰራር እንቅፋት የሆኑና ሪፎርሙን ወደ ኋላ የሚጎትቱ ጉዳዮችን ማስተካከል እንደሚገባ ያመላከቱት አፈ ጉባኤዋ፣ አብይ ኮሚቴውም በቀጣይ ተግባራቱን እየገመገመ አቅጣጫ እንደሚያስቀምጥ መግለፃቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review