በፓሪስ ኦሊምፒክ የመጀመሪያው የአበረታች ንጥረ ነገር ተጠቃሚ ተገኘ
AMN -ሐምሌ 20/2016 ዓ .ም
ትናንት ምሽት በጀመረው በፓሪስ ኦሊምፒክ የመጀመሪያው የአበረታች ንጥረ ነገር የተጠቀመ አትሌት መገኘቱ ይፋ ሁኗል።
የ28 ዓመቱ ኢራቃዊ የጁዶ ስፖርት ተወዳዳሪ ሳጃድ ሰሂን ምንነቱ ያልታወቀ አበረታች ቅመም ተጠቅሞ መገኘቱን ኢንተርናሽናል ቴስት ኤጀንሲ (ITA) ይፋ አድርጓል።
በጁዶ ስፖርት ኢራቅን ወክሎ ፓሪስ የተገኘው ሰሂን በተደረገለት ምርመራ በደሙ ውስጥ የአበረታች ንጥረ ነገር በመገኘቱ ከውድድሩ እንዲታገድ መደረጉን ኤጀንሲው ገሏጿል።
በዚህም አትሌቱ ለጊዜው በማንኛውም የስፖርት ውድድር እንዳይሳተፍና የኢራቅ የኦሎምፒክ ቡድን ካምፕን ለቆ እንዲወጣ መደረጉ ነው የተገለጸው።