በ17ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የምድብ ሁለተኛ ጨዋታዎች በዛሬው ዕለት መካሄድ ሲጀምሩ በምድብ አንድ ሀድያ ሆሳዕና ወደ ግማሽ ፍፃሜው ማለፉን አረጋግጧል።
በዛሬው ዕለት የምድብ አንድ ሁለት ጨዋታዎች የተከናወኑ ሲሆን መጀመሪያ ላይ በተደረገው ጨዋታ ሀዲያ ሆሳዕና ሻሸመኔ ከተማን በሬችሞን ኦዶንጎ ብቸኛ ግብ በማሸነፍ በስድስት ነጥብ ከወዲሁ ወደግማሽ ፍፃሜ መግባቱን ሲያረጋግጥ በጨዋታው ጥሩ የተንቀሳቀሰው የሀዲያ ሆሳዕናው በየነ ባንጃው የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
ኢትዮጵያ ቡና እና ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተገናኙበት የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ በሁለት አቻ ውጤት ተጠናቋል።
ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቢኒያም ጌታቸው እና አዲስ ግደይ ለኢትዮጵያ ቡና ደግሞ ብሩክ በየነ(በፍፁም ቅጣት ምት) እና አማኑኤል አድማሱ ግብ አስቆጥረዋል።
በጨዋታው የኢትዮጵያ ንግድ ባንኩ በረከት ይግዛው የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
የምድብ ሁለተኛ ጨዋታ ነገ የሚደረግ ሲሆን በምድብ ሁለት ኢትዮጵያ መድህን ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቀን 7:00 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
በአብርሃም አድማሱ
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!
YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr
Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9
Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8
Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ