AMN ታህሳስ -2/2017 ዓ.ም
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት ኢትዮጵያ የቡና መገኛ ብቻ ሳትሆን ከፍተኛ ቡና አምራች ሀገር ለማድረግ የተጀመሩ ሥራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል ብለዋል ፡፡
ባለፉት 5 ዓመታት የቡና ምርታማነትን ለማሳደግ በተከናወኑ ስራዎች ዓመታዊ የቡና ምርት መጠንን ከነበረበት 500 ሺህ ቶን በእጥፍ ማሳደግ መቻሉንም ገልፀዋል።
ከገቢ አንጻርም በተጠናቀቀው የ2016 በጀት ዓመት ከቡና ወጪ ንግድ ከ1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ የተገኘ ሲሆን፤ በተያዘው በጀት ዓመት ደግሞ ይህን አሃዝ ወደ 2 ቢሊዮን ዶላር ከፍ ለማድረግ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ነው።
እስካሁን ባለው ሂደትም እቅዱን ለማሳካት የሚያስችሉ አበረታች ውጤቶች ከወዲሁ እየተመዘገቡ ነውም ብለዋል።
ዘመናዊ የቡና መስኖ ልማትና በማሽን የታገዘ የቡና ለቀማ በማካሄድ በሄክታር እስከ 60 ኩንታል ማግኘት መቻሉ ደግሞ ለዚሁ ስኬት ጥሩ ማሳያ ነው ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸው።