AMN – ጥቅምት 14/ 2017 ዓ.ም
በ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ከወጪ ንግድ ከ1.5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ መገኘቱን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ አስታወቁ ፡፡
ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው በዛሬው ዕለት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የወጪ ንግድ (ኤክፖስርት) አፈጻጸምን ከላኪዎች ጋር ገምግመናል ብለዋል ።
አፈጻጸሙ በምርት ጭማሪም ሆነ በውጭ ምንዛሪ ዕድገት ካለፈው በጀት ዓመት አፈጻጸም ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ለውጥ መታየቱን ተመልክተናል።
ባለፉት ሶስት ወራት ከ1,5 ቢሊዮን ዶላር በላይ ገቢ እንደተገኘና ይህም የእቅዱን 132 በመቶ መሆኑን ሚኒስትሩ ገልጸዋል::
በዓመቱ ቀሪ ወራት ዕቅድ አፈጻጸማችንን በማላቅ ኢኮኖሚያችን የሚፈልጋውን የውጭ ምንዛሪ ግኝት ለማሳደግ ከዘርፉ ተዋናዮችና ከላኪዎቻችን ጋራ ወደ ጋራ መግባባት ላይ ደርሰናልም ብለዋል ።