AMN-ሰኔ 12/2016 ዓ.ም
በካሜሮን ዱዋላ ከተማ በሚደረገው በ23ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ላይ የሚካፈለው የኢትዮጵያ ልዑክ ቡድን በዛሬው ዕለት ወደ ካሜሮን ዱዋላ አቅንቷል ።
የኢ.አ.ፌ ምክትል ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ማስተዋል ዋለልኝ በቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በመገኘት ቡድኑን መሸኘታቸውን ከፌዴሬሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!