ባህላዊ እሴቶችን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የማጥናት፣ የመሰነድና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ነው

You are currently viewing ባህላዊ እሴቶችን ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የማጥናት፣ የመሰነድና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ ነው

AMN – ጥር 5/2017 ዓ.ም

ባህላዊ እሴቶች ለምተውና ተጠብቀው ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የማጥናት፣የመሰነድና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ባህል፣ ኪነ ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ገለጸ።

ቢሮው በባህል እሴቶችና ሀገር በቀል ዕውቀቶች፣በእደ ጥበብ ሃብቶችና ቋንቋ ዙሪያ በስሩ ለሚገኙ ከሁሉም የዘርፉ ባለድርሻ አካላትና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መስጠት ጀምሯል።

በቢሮው የባህል እሴቶች፣እደ ጥበብ ሃብቶችና ቋንቋዎች ልማት ዳይሬክተር ወይዘሮ አዳነች ካሳ እንደተናገሩት፤አዲስ አበባ የተለያዩ ብሔረ ብሔረሰቦች፣ባህሎችና ቋንቋዎች መገኛ መሆኗን ጠቅሰዋል፡፡

ባህላዊ እሴቶች ለሀገር ገጽታ ግንባታና ኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ በዘርፉ ላይ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

እነዚህን ባህላዊ እሴቶችን በማዘመንና ወደ እንዱስትሪው በማሸጋገር ከዘርፉ መገኘት የሚገባውን ጥቅም ለማግኘት እየተሰራ መሆኑንም ተናግረዋል።

በመሆኑም ባህላዊ እሴቶች ለምተውና ተጠብቀው ለመጪው ትውልድ ለማስተላለፍ የማጥናት፣ የመሰነድና የማስተዋወቅ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ቢሮ ዘርፉን ለማዘመንና ከወቅቱ ጋር መራመድ እንዲችል በዕደ ጥበብ፣ ስነ ጥበብና በተለያዩ ዘርፎች ላይ ዝንባሌ ያላቸውና ለተሰማሩ ዜጎች አጫጭር ስልጠናዎችን የማዘጋጀትና የመስጠት ስራ እየሰራ መሆኑን አክለዋል፡፡

ስልጠናው ሰልጣኞች በዘርፉ ያላቸውን ዕውቀትና ክህሎት ለማዳበርና ያለመ መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

አቶ አየለ ዘሪሁንና አቶ ተስፋዬ ሺፈራው የስልጠናው ተሳታፊዎች ሲሆኑ ስልጠናው ስራችንን በዕውቀትና በክህሎት እንድንሰራ መነቃቃት የሚፈጥር ነው ማለታቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review