ባለስልጣኑ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ በለቀቁ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የገንዘብ ቅጣት እርምጃ ወሰደ

You are currently viewing ባለስልጣኑ ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ በለቀቁ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ላይ የገንዘብ ቅጣት እርምጃ ወሰደ

AMN – መጋቢት 3/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ጋር በመተባበር ፍሳሽ ቆሻሻ ወደ ወንዝ የለቀቁ ድርጅቶችና ግለሰቦችን በደንብ ቁጥር 180/2017 መሰረት የገንዘብ ቅጣቶች በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን ገለጸ፡፡

ባለስልጣኑ በዛሬው እለት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 1,800,000 ብር፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ 1,750,000 ብር፣ በአራዳ ክፍለ ከተማ 1,200,000 ብር፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ 600,000 ብር፣ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 400,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ መውሰዱን አስታውቋል፡፡

በተያያዘም በቦሌ ክፍለ ከተማ 450,000 ብር፣ በኮልፌ ክፍለ ከተማ 400,000 ብር፣ በልደታ ክፍለ ከተማ 100,000 ብር በመቅጣት አስተዳደራዊ እርምጃ በመውሰድ ለመንግስት ገቢ አድርጓል።

ባለስልጣኑ በአጠቃላይ በዛሬው እለት በ24 ጅርጅቶች እና በ3 ግለሰቦች በድምሩ 6,700,000/ስድስት ሚሊየን ሰባት መቶ ሺህ/ ብር መቅጣቱን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለስልጣን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review