ባለፈው በጀት አመት ከ19ሺ በላይ ህጻናትን ከጉልበት ብዝበዛ መታደግ መቻሉ ተመላከተ

You are currently viewing ባለፈው በጀት አመት ከ19ሺ በላይ ህጻናትን ከጉልበት ብዝበዛ መታደግ መቻሉ ተመላከተ

AMN – ሰኔ 12/2017 ዓ.ም

ከ72 ሚሊየን በላይ አፍሪካዊያን ህጻናት የጉልበት ብዝበዛ ሰለባ ሲሆኑ ከዚህ ውስጥ 31.5 የሚሆኑን በአስከፊ ሁኔታ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃዎች ያሳያሉ።

ሐገራችን ኢትዮጵያ ደግሞ ከቡርኪና ፋሶና ሶማሊያ ቀጥላ 3ኛ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ የሚፈጸምባት ሐገር ስትሆን ወደ 43 በመቶ የሚጠጉት ኢትዮጵያውያን ህጻናት የጎልበት ብዝበዛ ሰለባ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ።

የአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛን ለማስቆም ጥረታችንን እናፋጥን በሚል መሪ ሐሳብ የህፃናት ቀንን አክብሯል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ ንግግር ያደረጉት በአዲስ አበባ ስራና ክህሎት ቢሮ የአሰሪና ሰራተኛ ጉዳይ ዘርፍ ኃላፊ አቶ አበበ ተቀባ፤ የህጻናት ጉልበት ብዝበዛ በግለሰብ ደረጃ ከሚያደርሰው ስብስብ ስነ-ልቦናዊ፣ አካላዊና ማህበራዊ ቀውሶች ባሻገር እንደ ሐገርም የሚያስከትለው ተጽእኖ ከፍተኛ መሆነን ጠቁመዋል።

የነገ ብቁ ሐገር ተረካቢ ትውልድን ለመፍጠር የህጻናትን ሰብአዊ መብት በተሟላ ሁኔታ ማስከበር ይገባናል ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከህጻናት መብት ጥበቃ ጋር ተያይዞ የተለያዩ ስምምነቶችን ብትፈርምም ተግባራዊነቱ ላይ ክፍተቶች አሉ ያሉት ኃላፊው የግንዛቤ ስራዉን ጨምሮ የተቀናጀ ስራ ያስፈልጋል ብለዋል።

በሐገራችን ብሎም በአፍሪካ ደረጃ 85 በመቶ በህጻናት ላይ የሚፈፀሙ የጉልበት ብዝበዛዎች በግብርናው የስራ መስክ የሚፈጸም ሲሆን የአገልግሎትና ኢንደስትሪ ዘርፎች በቅደም ተከተል ይከተላሉ።

በመዲናችን አዲስ አበባ ከ5 በመቶ በላይ ህጻናት የጉልበት ብዝበዛ የሚፈጸምባቸው ሲሆን ንፋስ ስልክ ቂርቆስ ክፍለ ከተሞች በብዛት የጉልበት ብዝበዛ የሚፈጸምባቸው መሆኑ ተገልጿል።

ባለፈው በጀት አመት ከ19ሺ በላይ ህጻናትን ከጉልበት ብዝበዛ መታደግ መቻሉ በመድረኩ ተመላክቷል።

በሔኖክ ዘነበ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review