ባለፉት ሶስት ወራት በሸገር ዳቦና በመንግስትና ባለሀብት ጥምረት በተገነቡ ዳቦ ቤቶች ከ84 ሚሊየን በላይ ዳቦ ለህብረተሰቡ ቀርቧል- ንግድ ቢሮ

You are currently viewing ባለፉት ሶስት ወራት በሸገር ዳቦና በመንግስትና ባለሀብት ጥምረት በተገነቡ ዳቦ ቤቶች ከ84 ሚሊየን በላይ ዳቦ ለህብረተሰቡ ቀርቧል- ንግድ ቢሮ

AMN – መስከረም 21/2017 ዓ.ም

በባለፉት ሶስት ወራት በሸገር ዳቦና በመንግስት ባለሀብት ጥምረት በተገነቡ ዳቦ ቤቶች ከ84 ሚሊየን 795 ሺህ በላይ ዳቦ መሰራጨቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ ገልጿል፡፡

በቢሮው የንግድ ግብይት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መከታው አዳፍሬ እንደገለፁት፣ በከተማ አስተዳደሩ ድጎማ የሚደረግበት ዳቦ በበቂ አቅርቦትና ጥራት ለህብረተሰቡ እንዲሰራጭ እየተደረገ ይገኛል ብለዋል፡፡

በከተማዋ ዝቅተኛ የዳቦ ግራም 70 ግራም መሆኑን የገለጹት አቶ መከታው የሸገር ዳቦ በ5ብር እንዲሁም በመንግስት ባለሀብት ጥምረት በተገነቡ ዳቦ ቤቶች የሚቀርቡት ደግሞ በ6ብር እንዲሰራጩ እየተደረገ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ከዳቦ ግራምና ዋጋ ቁጥጥር አኳያም ከ70ግራም በታች ዳቦ በመጋገር ለሽያጭ የሚያቀርቡ ተቋማት ላይ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የእርምት እርምጃ እየተወሰደ መሆኑን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review