ባለፉት አምስት ዓመታት ከሀገር ወጥተው የነበሩ ከ70 በላይ ቅርሶችን ማስመለስ ተችሏል- ባለስልጣኑ

You are currently viewing ባለፉት አምስት ዓመታት ከሀገር ወጥተው የነበሩ ከ70 በላይ ቅርሶችን ማስመለስ ተችሏል- ባለስልጣኑ

AMN – ጥር 20/2017 ዓ.ም

ባለፉት አምስት ዓመታት በተለያዩ ጊዜያት ከሀገር የወጡ ከ70 በላይ ቅርሶች ወደ ሀገር ቤት እንዲመለሱ መደረጉን የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ገለፀ።

ምድረ ቀደምት ሀገር ኢትዮጵያ አይነተ ብዙ ተፈጥሯዊና ሰው ሰራሽ ቅርሶች ባለቤት ስትሆን በርካታ ቅርሶቿም በዓለም ቅርስነት ተመዝግበዋል።

በሌላ በኩል ኢትዮጵያ ተንቀሳቃሽ ታሪካዊ ቅርሶቿ በተለያዩ ዘመናት ከሀገር እየተዘረፉ ወጥተው በተለያዩ አገራት፣ ተቋማትና ግለሰቦች ዕጅ ይገኛሉ።

በየክፍላተ ዓለሙ የሚገኙ ቅርሶችን ለማስመለስ የሀገር ተቆርቋሪ ምሁራን፣ ተፅዕኖ ፈጣሪና ታዋቂ ሰዎችን ያቀፈ የኢትዮጵያ ቅርሶች አስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴ ተዋቅሮ ሁሉን አቀፍ ጥረት አድርጓል።

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ረዳት ፕሮፌሰር አበባው አያሌው እንዳሉት ባለስልጣኑ ከተንቀሳቃሽ ቁስ እስከ ታሪካዊ ስነ ሕንጻዎችን ጥበቃና ልማት ስራዎችን እያከናወነ ነው።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) ሀሳብ አመንጪነት የሚከናወኑ የብሔራዊ ቅርሶች ዕድሳትን ጨምሮ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች የቅርሶችን ጥበቃ፣ ዕደሳትና ጥገና እየተደረገ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ከቅርስ ጥበቃና ልማት ባሻገር በየዘመናቱ ከሀገር የወጡ ቅርሶችን ለማስመለስ በመንግስትና በብሔራዊ ኮሚቴው የተደረገውን ጥረትም ጠቅሰዋል።

በዚህም ባለፉት አምስት ዓመታት ብቻ በተለያዩ ጊዜያት ከሀገር የወጡ ከ70 በላይ ቅርሶችን ማስመለስ እንደተቻለ ተናግረዋል።

ቅርሶች ከማንነትና ታሪካዊ መገለጫነታቸው ባሻገር ለቱሪዝም ኢኮኖሚ እመርታ ሁለንተናዊ ፋይድ ያላቸው የሀገር ውድ ሀብቶች መሆናቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

Ethiopia

Addisababa

Ethiopia

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review