ባለፉት 4 አመታት የወጪ ንግድ ዘርፉ በአማካይ 7 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለፀ

You are currently viewing ባለፉት 4 አመታት የወጪ ንግድ ዘርፉ በአማካይ 7 በመቶ እድገት ማሳየቱ ተገለፀ

አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 7/2016 ዓ.ም

በኢትዮጵያ ባለፉት 4 አመታት የወጪ ንግድ ዘርፉ ላይ በትኩረት በመሰራቱ በአማካኝ በ7 በመቶ ዉጤት ማስመዝገብ መቻሉን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከውጭ ንግድ ዘርፎች ውስጥ የግብርና ዘርፍ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበረው ተገልጿል፡፡

ከግብርናው ዘርፍ በዋነኝነት ቡና የቅባት እህሎችና አበባ እንዲሁም ጫት የሚጠቀሱ ሲሆን የቡና እና አበባ ምርቶች ከታቀደው በላይ ትርፍ የታየባቸው ዘርፎች ናቸውም ተብሏል፡፡

በሁለተኛ ደረጃ የማዕድን ዘርፍ ጥሩ የሚባል እድገት እያሳየ ያለ ዘርፍ ሲሆን ወርቅ ወደ ውጭ በማቅረብ ዉጤት እየተመዘገበ እንደሚገኝ ተመልክቷል፡፡

በማኑፋክቸሪንግ ዘርፍ ላይ የጨርቃ ጨርቅ ምርቶች በሶስተኛ ደረጃ ለውጪ ገበያ እየቀረቡ መሆኑን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በተጨማሪም ባለፉት 4 አመታት የአገልግሎት ወጪ ንግድ ላይ እድገት መታየቱ ተገልጿል፡፡

በአገልግሎት ዘርፍ በ2012 ዓ.ም 4.69 ቢሊየን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ የነበረ ሲሆን 4.7 ቢሊየን ዶላር አፈፃፀም መመዝገቡ ተጠቅሷል፡፡

በእቅዱ ማብቂያ አመት በ2015 6.07 የታቀደ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን 7.1 መገኘት መቻሉም ተመላክቷል፡፡

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr

Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9

Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8

Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review