ባለፉት 6 ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ55 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ተገኝቷል-የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

You are currently viewing ባለፉት 6 ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ55 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ተገኝቷል-የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን

AMN-ጥር 18 /2017 ዓ.ም

የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን በሚያስተዳድራቸው ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖችና የድሬዳዋ ነጻ ንግድ ቀጠና ውስጥ በበጀት ዓመቱ የመጀመሪያ 6 ወራት ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከ55 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ማግኘቱን ገልጿል፡፡

የኮርፖሬሽኑ የኦፐሬሽን ዘርፍ ስራ አስፈጻሚ ካሚል ኢብራሂም እንደገለጹት፣ ባለፉት 6 ወራት ከ72 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር በላይ ወደ ውጭ ለመላክ አቅዶ የእቅዱን 73 በመቶ ማሳካት ችሏል፡፡

ቦሌ ለሚ፤ሃዋሳ እና አዳማ ልዩ የኢኮኖሚ ዞኖች ወደ ውጭ ከተላኩ ምርቶች ከፍተኛውን ደረጃ የያዘ ሲሆን አልባሳትና ጨርቃጨርቅ ከፍተኛውን ድርሻ መያዙም ተገልጿል፡፡

በኮርፖሬሽኑ በመጀመሪያው 6 ወራት ውስጥ ከ24ሺ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል እንዲሁም የሃገር ውስጥ አምራቾችን ከውጭ ሃገር አምራቾች ጋር በተፈጠረ የገበያ ትስስር ከ35 ነጥብ 7 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘት መቻሉን ከኮርፖሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review