ባለፉት 6 ወራት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚገመት የመንግስትን መብትና ጥቅም ማስከበር ተችሏል፡-ፍትህ ቢሮ

You are currently viewing ባለፉት 6 ወራት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚገመት የመንግስትን መብትና ጥቅም ማስከበር ተችሏል፡-ፍትህ ቢሮ

AMN- ጥር 20/2017 ዓ.ም

ባለፉት 6 ወራት 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚገመት የመንግስትን መብትና ጥቅም ማስከበር መቻሉን የአዲስ አበባ ከተማ ፍትህ ቢሮ አስታወቀ::

ቢሮው የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ 6 ወራት አፈፃፀሙን በቢሾፍቱ እየገመገመ ነዉ።

ቢሮው ለአስተዳደሩ የህግ ጉዳዮች ዋና አማካሪና ተወካይ ሆኖ እንዲሠራ በአዋጅ ኃላፊነት እንደተሰጠው ይታወቃል::

በዚህም ባለፉት 6 ወራት በፍትሐ ብሔር ከቀረቡ 4 ሺህ 741 የክስ መዝገቦች ውስጥ 1 ሺህ 895 መዝገቦችን ዉሳኔ እንዲያገኙ አድርጓል ፡፡

ከነዚህ ውስጥም 1 ሺህ 766 መዝገቦች ዉሳኔ እንዲያገኙ በማድረግ 1 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር የሚገመት የአስተዳደሩን መብትና ጥቅም ማስከበር መቻሉ ተገልጿል::

ቢሮው በወንጀል ጉዳዮች ከቀረቡ 7 ሺህ 852 የምርመራ መዝገቦች ሁሉም ዉሳኔ እንዲያገኙ ማድረጉ ተመላክቷል::

የነዋሪውንና የአስፈጻሚ አካላትን ንቃት ህግ ለማስደግ በተከናወኑ ተግባራት አስተዳደሩ የጀመረውን የተቌማት ሪፎርም እንዲሳካ ሚናው የጎላ እንደነበር በመድረኩ ተገልጿል::

በአንዋር አህመድ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review