ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ የሚገኙ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 6/2016 ዓ.ም

You are currently viewing ብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች በአዳማ ከተማ የሚገኙ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኙ አዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ(ኤ ኤም ኤን )መስከረም 6/2016 ዓ.ም

የፌዴራል እና የክልል የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች “ሃብት መፍጠር እና ማስተዳደር” በሚል መሪ ሐሳብ በአዳማ ከተማ የሚገኙ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን ጎብኝተዋል።

የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮች ”ከዕዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ የተዘጋጀው የመጀመሪያ ዙር ሥልጠና በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በሥልጠናው ላይ ከፌዴራል እና ከሁሉም ክልሎች የተወጣጡ ከፍተኛ አመራሮች እየተሳተፉ ሲሆን በዛሬው ዕለትም በአዳማ ከተማ የሚገኙ ትላልቅ ኢንዱስትሪዎችን ጎበኝተዋል።

ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎቹ ሥልጠናው ትልቅ አቅም እንደሚፈጥር ገልጸው፣ በጉብኝታቸውም የኢትዮጵያን እምቅ ሃብቶች መጠቀም እና በአግባቡ የማስተዳደር ሂደቶችን መገንዘባቸውን ተናግረዋል።

የገንዘብ ሚኒስትሩ አሕመድ ሺዴ እና የፕላን እና ልማት ሚኒስትሯ ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር)፤ በሁሉም መስክ ያሉ የኢትዮጵያ እምቅ ሃብቶችን በአግባቡ ተረድቶ ጥቅም ላይ ማዋል እንደሚገባ ተናግረዋል።

ኃላፊዎቹ በጋራ አልምቶ መጠቀም እና በተገቢው መንገድ ማስተዳደር እንደሚገባም ነው የገለጹት።

በጉብኝታቸው ኢትዮጵያን የሚያሻግሩ በርካታ የልማት ክንውኖች መኖራቸውን እንዳዩ ጠቅሰው፣ የሀገሪቷን ዕድገት እና ብልጽግና ለማረጋገጥ አመራር ጨምሮ የሕዝቡ ትብብርና የጋራ ልማት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በፋብሪካዎች የተመለከትናቸው ሀብት የመፍጠር እና የማስተዳደር ልምድ እንዲሁም እንደ ሀገር ሀብቶችን በአግባቡ ማወቅ፣ መጠቀም እና ማስተዳደር የሚቻልበትን ሁኔታ ነው ብለዋል።

የንግድ እና ቀጣናዊ ትሥሥር ሚኒስትሩ ገ/መስቀል ጫላ እና የገቢዎች ሚኒስትሯ አይናለም ንጉሴ በበኩላቸው በሥልጠናው እና በጉብኝቱ የመንግሥትን የልማት ፖሊሲዎች በአግባቡ በመተግበር ሀገርን ወደ ተሻለ ምዕራፍ ለማሸጋገር የአመራሩ ቁርጠኝነት ወሳኝ መሆኑንም ተገንዝበናል ብለዋል።

“ከእዳ ወደ ምንዳ” በሚል መሪ ሐሳብ እየተሰጠ ባለው ሥልጠናም ኢትዮጵያ ጸጋዎቿን በመጠቀም ለቀጣዩ ትውልድ እዳን ሳይሆን ምንዳን ለማስተላለፍ አመራሩ ሌት ተቀን መሥራት እንዳለበት የጋራ አቋም የወሰድንበት ነው ያሉት።

ሀገራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ተለዋዋጭ ሁኔታዎችን በአግባቡ ተገንዝቦ ፈተናዎችን ወደ ዕድል በመቀየር ለአገር ዕድገትና ለሕዝቦች ተጠቃሚነት በጋራ የሚያነሳሳ ሥልጠና መሆኑንም ጠቅሰዋል።

የክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች እና ከፍተኛ አመሮችም፤ ኢትዮጵያ ሰፊ የመልማት አቅም ያላት በመሆኑ በየአካባቢው ያሉ እምቅ ሃብቶችን በማልማት ወደ ሀገራዊ ሃብት መቀየር አነደሚገባ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የዋና ጽህፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህ፤ የብልጽግና ፓርቲ ለሕዝቡ የገባውን ቃል ማስፈፀም የሚያስችል የአመራር አቅም የመፍጠርና ዓላምን የሰነቀ ሥልጠና መሆኑን መግለፃቸው ይተወሳል።

ፓርቲው ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋጥ በሚያደርገው ጥረት በተለይም የአመራሩ የአስተሳሰብ እና የተግባር አንድነት ወሳኝ መሆኑንም አስገንዝበዋል።

በመሆኑም በየደረጃው ያሉ አመራሮችን በሥልጠና አቅም የመገንባት ሥራ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አረጋግጠዋል።

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

YouTube ➲ http://bit.ly/3itThRr

Telegram ➲ http://bit.ly/3W4puw9

Facebook ➲ https://bit.ly/3CJVgI8

Twitter ➲ http://bit.ly/3IKQ3TZ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review