ብልፅግና ፓርቲ በብዙ መንገድ ተስፋ የሚጣልበት፣ ለአፍሪካም ምሳሌ የሚሆን ሀገር በቀል ፓርቲ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

You are currently viewing ብልፅግና ፓርቲ በብዙ መንገድ ተስፋ የሚጣልበት፣ ለአፍሪካም ምሳሌ የሚሆን ሀገር በቀል ፓርቲ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ

AMN – ግንቦት 30/2017 ዓ.ም

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ጋር ባደረጉት ቆይታ የብልፅግና ፓርቲን ቁመና በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማብራሪያቸውም የብልፅግና ፓርቲ ተአምራዊ ፓርቲ እንደሆነ እና በሀገራችን እስካሁን ከነበሩ ፓርቲዎች ሁሉ በስያሜው፣ በመጠኑም፣ በአደረጃጀቱም፣ በሀሳቡም፣ በተግባሩ እና በራዕዩ ጭምር ከብዙዎች ፓርቲዎች የተለየ ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ኢትዮጵያዊያን በዘርና በሰፈር ሳይከፋፈሉ፣ ሁሉንም አቅፎ የያዘ ፓርቲ መሆኑን ያመላከቱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ በርካታ አባላት ያሉት በአፍሪካ ትልቁ ፓርቲ መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የብልፅግና ፓርቲ ትልቅ ራዕይ፣ ግልፅ ፕሮግራም እና ስርዓት ያለው፣ በራሱ እሳቤዎች የሚመራ፣ አባላቱ በሀሳብ ተግባብተው ወደ ስራ የሚሰማሩበት እና በውጤት የሚከሰቱበት ፓርቲ እንደሆነም ነው ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ያብራሩት፡፡

ብልፅግና በጣም ክፍት የሆነ ፓርቲ በመሆኑ ከውጭ መጥተው፣ ፓስፖርታቸውን ቀይረው፣ የሌላ የፖለቲካ ፓርቲ አባል የነበሩ ሰዎች ሳይቀሩ ወደ ብልፅግና መቀላቀላቸውንም ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አክለውም ብልፅግና ፓርቲ በብዙ መንገድ ተስፋ የሚጣልበት፣ ለአፍሪካ ምሳሌ የሚሆን የራሱን ሀሳብ ያፈለቀ፣ በማንም ርዕዮተ ዓለም ያልታሰረ፣ ከሰዎች የተማረ እና ራሱን የገነባ ከብዙዎች ፓርቲዎች የተለየና የሚያጓጓ ሀገር በቀል ፓርቲ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review