ተመድ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ለተመረጡት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፈ

You are currently viewing ተመድ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ለተመረጡት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላለፈ

AMN – መስከረም 28/2017 ዓ.ም

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሆነው ለተመረጡት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የእንኳን ደስ ያለዎት መልዕክት አስተላልፏል።

ኢትዮጵያ እና ተመድ ለረጅም ጊዜ የቆየ አጋርነት እንዳላቸው የገለጸው ድርጅቱ በኢትዮጵያ አገር በቀል መፍትሔዎችን መሰረት በማድረግ የልማት ስራዎችን እየደገፈ እንደሚገኝም አስታውቋል፡፡

ኢትዮጵያ ዘላቂ የልማት ግቦቹን ለማሳካት እያደረገች ያለውን ጥረት መደገፉን እንደሚቀጥልም አረጋግጧል፡፡

የቀድሞ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ለሁለቱ ወገኖች የጋራ ትብብር መጠናከር ላደረጉት አስተዋጽኦም ምስጋና አቅርቧል፡፡

ትብብሩን ከአዲሱ የኢፌዴሪ ፕሬዝደንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ድርጅቱ በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ባወጣው የመልካም ምኞት መግለጫ አስታውቋል፡፡

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review