ተቋማዊ አሰራርን በማዘመንና ምቹ በማድረግ ትኩረት ሰጥተን በመስራታች ጥሩ አፈጻጸም አስመዝግበናል:- አቶ ጃንጥራር አባይ

AMN- ጥር 15/2017 ዓ.ም

የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ባለፉት 6 ወራት ታቅደው በተከናወኑ አበይት ተግባራት እና የሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርጓል።

በውይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሀላፊ አቶ ጃንጥራር አባይ እንደገለጹት ተቋማዊ አሰራርን በማዘመንና ምቹ በማድረግ ትኩረት ሰጥተን በመስራታች ባለፋት ስድስት ወራት ጥሩ አፈጻጸም ማስመዝገብ ችለናል ብለዋል።

የአምራች ኢንዱስትሪዎችን ምርትና ምርታማነት ለማሳደግ መመሪያዎችን በመከለስ፣ አሳታፊ የሆነ ስራን ለመስራት፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ ተሻጋሪ የሆነ ውጤት ለማምጣት ትኩረት ሰጥተው እንደሚሰሩ አቶ ጃንጥራር አባይ ተናግረዋል።

ወጥነት ያለው እቅድን በመከለስ፣ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ፣ ጥራት ያለው መረጃ በመያዝ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀምን በማሳደግ እንዲሁም የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ አቶ ጃንጥራር አሳስበዋል።

ጥራት ያለው እቅድ በማዘጋጀት፣ የአቅም ግንባታ ስልጠና በመስጠት፣ በየደረጃው ያለው አመራርና ባለሙያ ተናቦ በመስራት፣ ከባለድርሻ አካላት ጋር ቅንጅታዊ አሰራርን በማሳደግ እንዲሁም ሙያዊ ድጋፍ በማድረግ የአምራች ኢንዱስትሪዎች ምርትና ምርታማነት በማሳደግ በሀገር ደረጃ ያላቸውን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ማሳደግ መቻሉንም በቢሮ ኃላፊ ደረጃ የፋሲሊቴሽንና የካይዘን ትግበራ ዘርፍ ኃላፊ ኤፍሬም ግዛው (ዶ/ር) መግለፃቸውን ከቢሮው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

All reactions:

1111

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review