ተናፋቂዎቹን በዓላት በተዋቡ አደባባዮች

አዲስ አበባ እንደ ንስር ታድሳ፣ እንደ መስከረም ፀሐይ ደመናውን ጥሳ፣ እንደ አደይ አበባ ውበትን ተላብሳ የብዙዎችን ቀልብ እየሳበች እንደሆነ አለም አቀፍ ተቋማት ሳይቀሩ በመመስከር ላይ ናቸው። በቅርቡ የኢኮኖሚስት ኢንተለጀንስ ዩኒት “የአፍሪካ ከተሞች በ2035” በሚል ርዕስ ይፋ ያደረገውን መረጃ በዋቢነት መጥቀስ ይቻላል፡፡ በዚሁ መረጃ መሰረት አዲስ አበባን ጨምሮ ስድስት ከተሞች በ2035 ወደ ሜጋ ከተማነት እንደሚያድጉ አስታውቋል። ይህ ግምት የተሰጣቸው አዲስ አበባ፣ ብራዛቪል፣ ዳሬሰላም እና ሩዋንዳ ናቸው። ዕድገቱ የመሠረተ ልማት ዝርጋታን፣ የከተሞች መስፋፋት እና በአቅራቢያ ያሉ የትላልቅ ከተሞች መፈጠር እንደሚያካትት ሪፖርቱ ያመላክታል።

በርግጥም ስለ አዲስ አበባ አስገራሚ ለውጥ ለመናገር ምስክር አያሻም፤ ምክንያቱም ከተማዋ እንደስሟ አበባ እየሆነች ስለመምጣቷ የተመለከታት ሁሉ ምስክር ነው ይላሉ የመዲናዋ ነዋሪ አቶ አህመድ ከማል፡፡ በመዲናዋ ከ35 አመታት በላይ እንደኖሩ የነገሩን አቶ አህመድ እንደሚሉት ከተማዋ ቀደም ባሉት ዘመናት ነግዶ ለማትረፊያ እንጂ ያን ያህል ለመኖሪያ ምቹ አልነበረችም፡፡ ምክንያቱም ንፅህናቸውን ያልጠበቁ መንገዶችና መንደሮች በብዛት ከመኖራቸውም በላይ በአንዳንድ አካባቢዎች ክረምት በመጣ ቁጥር አሊያም ሙቀቱ በሚያይልባቸው ወቅቶች ወረርሽኞች ጭምር ይከሰቱ እንደነበር አስታውሰው፣ አሁን በከተማዋ እየተከናወነ ባለው ልማት እነዚህ ችግሮች እየተፈቱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

አሁን ግን ከተማዋ ለንግድ ብቻ ሳይሆን ለመኖሪያም የምትመረጥ፣ ጎዳናዎቿ የሚያምሩ ውብ ሆናለች፡፡ በዚህ ላይ ህዝቡ በነቂስ ወጥቶ በዓላቱን ሲያከብር ከህብረ ቀለማቱ ውበት ጋር የተዳመረ ገፅታዋ ጎልቶ ሲወጣ እጅጉን ታምራለች ይላሉ አቶ አህመድ፡፡

ወይዘሮ ስንቅነሽ ማሩ በበኩላቸው የአዲስ አበባ ውበት ነግቶ በጠባ ቁጥር አዲስ እየሆነ ነው። ከመዋባቸው የተነሳ አንዳንድ የማውቃቸው ስፍራዎች ጭምር ግር እያሉኝ መጥተዋል ይላሉ። ይህን መሰል ለውጥ ከእኛ ባሻገር ለልጆቻችን እና ለልጅ ልጆቻችን ትልቅ ሀብት እንደማስቀመጥ ነው፡፡ በተለይም የመስቀል፣ የኢሬቻ እና መሰል በዓላትን በአደባባይ ወጥተን ስናከብር የበለጠ ያምራል ይላሉ፡፡

የኮሪደር ልማቱ እንደ መስቀልና ኢሬቻ ላሉ የአደባባይ በዓላት ተጨማሪ ድምቀትን ፈጥሯል

በሐሮማያ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋና ባህል ጥናት ትምህርት ክፍል ተባባሪ ፕሮፌሰር ኢማና በየነ (ዶ/ር) እንደሚሉት፣ በኢትዮጵያ የሚከበሩ የአደባባይ በዓላት በዛ ያሉ ቢሆኑም የመስቀል ደመራ፣ ኢሬቻ እና ጥምቀት በበርካታ የሀገሪቱ ክፍሎች በድምቀት የሚከበሩና የማህበረሰቡን እሴት በጉልህ የሚያንፀባርቁ ናቸው፡፡ እነዚህ በዓላት በተለይ በአዲስ አበባ አደባባዮች የሚከበሩ ሲሆን፣ ህብረብሄራዊነት ነፍስ ዘርቶ የሚታይበት፣ የማህበረሰቡ የተለያዩ ባህላዊ አልባሳትና ጭፈራዎች እንዲሁም ልዩ ልዩ ባህላዊ ክዋኔዎች በመዲናዋ አደባባይ የኢትዮጵያዊያንን መልክና ልክ አጉልተው ሲያሳዩ የበርካታ ጎብኝዎችን ቀልብ ይስባሉ፡፡

አሁን ደግሞ አዲስ አበባ እንደ አዲስ ውበቷ እየፈካች፣ ጎዳናዎቿ እንደ ፅጌሬዳ አበባ የሚያሳሱ እየሆኑ መጥተዋል፡፡ ታዲያ በእነዚህ ውብ ጎዳናዎችና አደባባዮች ላይ መስቀል፣ ኢሬቻና የመሳሰሉት የአደባባይ በዓላት ሲከበሩ ለከተማዋ ተጨማሪ ውበትን ለበዓላቱም ድርብ ድምቀትን ይሰጣሉ፡፡

ኃይማኖታዊም ሆነ የህዝብ በዓላት ህዝቡ በክት ልብሱ ደምቆ፣ መልካም መንፈስን ታጥቆ እና ከቤቱ ወጥቶ የሚያከብራቸው በዓላት በመሆናቸው በህብረ ቀለማት ያሸበረቁ ናቸው። ቀደም ሲል በበዓላቱ ህብረ ዝማሬ እና ውብ ጭፈራዎች ይደምቁ የነበሩት አደባባዮች አሁን በኮሪደር ልማቱ ተጨማሪ ውበትን ተጎናፅፈዋል። ታዲያ የበዓላቱና አደባባዮቹ ድምቀት አብሮ ሲደመር ለከተማዋ ትልቅ ፍካትን ይፈጥራሉ። የማህበረሰቡም የነበሩ መልካም እሴቶች እንዲጎለብቱም ዕድል ይሆናሉ ይላሉ ኢማና (ዶ/ር)።

የኢትዮጵያዊያን ውብ ባህላዊ እሴቶች እንዲህ ደምቀው በአደባባይ ሲታዩ ለሌላው ዓለም የህዝቡን መልካም ገፅታ እንዲሁም የሀገርን ሁለንተናዊ ከፍታ ያሳያሉ፡፡ እየለማ ያለው ግዑዝ የሆነው ቦታ ብቻ ሳይሆን የማህበረሰቡም ነባር እሴት በመሆኑ በማህበራዊ፣ በኢኮኖሚያዊም ሆነ በፖለቲካዊ ዘርፎች ያለው ፋይደ ከፍ ያለ ስለመሆኑም ጠቅሰዋል፡፡

አዲስ አበባ አስደናቂ ለውጥ እያስመዘገበች ያለች ሲሆን፣ ለዚህ ለውጥ በዋቢነት የሚነሳው የኮሪደር ልማት ፕሮጀክት ነው። ይህ ታላቅ ተነሳሽነት የከተማዋን አካላዊ ገጽታ በመቅረጽ ብቻ ሳይሆን ህዝባዊ በዓላት በሚያምሩ ጎዳናዎች እንዲከበሩና ከፍ ብለውም እንዲታዩ በር የከፈተ ነውም ብለዋል፡፡

የኮሪደሩ ልማት የአዲስ አበባን መሠረተ ልማት ለማዘመን እና የበለፀገ የባህል ቅርሶቿን በመጠበቅ ላይ ያለመ የከተማ ፕላን ፕሮጀክት ስለመሆኑ የገለፁት ኢማና (ዶ/ር)፣ ልማት አዳዲስ መንገዶችን፣ መናፈሻዎችን እና የህዝብ ቦታዎችን መገንባትን ያጠቃልላል፡፡ ይህም ይበልጥ የተቀናጀ እና ተደራሽ የከተማ አካባቢ ይፈጥራል። ከመሰረተ ልማት ባሻገርም ከተማዋ ኃይማኖታዊም ሆነ ባህላዊ በዓላትን በከፍታቸው ልክ የማስተናገድ አቅም እንዲኖራት ያደርጋሉም ብለዋል፡፡

በርካታ ህዝብ የሚሰበሰብባቸው እና ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችና ቱሪስቶች የሚጎርፉባቸው እንደ መስቀል እና ኢሬቻን የመሳሰሉ በዓላትን የሚታደሙ የህብረተሰብ ክፍሎች ሳይጨናነቁ ባማሩ መንገዶችና አደባባዮች ደስታቸውን በኩራት የሚገልፁበትን ዕድል ያገኛሉ፡፡ ይህም በማህበረሰቡ ዘንድ የበለጠ እርካታን ከመፍጠሩ በላይ ለባህልና ወጉ ያለው ፍቅርና አክብሮት እንዲጎለብት ያደርጋል፡፡

የመስቀል ደመራ ዕለት፣ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስዱ የመዲናዋ መንገዶች በተለያዩ አልባሳት ተውበው እና በያሬዳዊ ዜማ ታጅበው በሚነጉዱ የበዓሉ ታዳሚዎች እንደሚደምቁ አስታውሰው፣ አሁን ደግሞ የመዲናዋ መንገዶች በኮሪደር ልማት እጅግ በመዋባቸው የደመራው በዓል ከመቼውም ጊዜ ለየት ባለ መልኩ ደማቅ ገፅታ ይኖረዋል ሲሉ አክለዋል፡፡

የኢሬቻ በዓል ከገዳ ሥርዓት ጋር ጥብቅ ቁርኝት ያለው ሲሆን፣ በኦሮሞ ማኅበረሰብ ዘንድ ለዘመናት ሲከበር  የቆየ ነው፡፡ በዋናነት ግን በአዲስ አበባ ሆራ ፊንፊኔ፣ በቢሾፍቱ ከተማ ደግሞ የሆራ ሃር-ሰዲ ከመስቀል በዓል በኋላ ባሉት ቅዳሜ እና እሁድ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ በታደመበት እንደሚከበር አስታውሰው፣ በበዓላቱ የማህበረሰቡ ልዩ ልዩ እሴቶች ይንፀባረቁበታል። በተለይም ባህላዊ አልባሳት ከነ ጭፈራቸው በአደባባዮቹ ሲታዩ እጅግ ያምራሉ፡፡ አሁን ደግሞ በኮሪደር ልማቱ የመዲናዋ መንገዶችና አደባባዮች በርካታ ህዝብ እንዲይዙ ከመደረጋቸውም በላይ በአረንጓዴ ልማት እና በዘመናዊ መልኩ ተውበዋል፡፡ በዚህ ላይ የኢሬቻ በዓል ታዳሚዎች ሲታከሉበት ከምንጊዜውም በበለጠ መልኩ በዓሉ ውብ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል፡፡

የአንትሮፖሎጂ ባለሙያው ገመቹ መገርሳ ለቢቢሲ እንደገለፁት፣ በኢሬቻ በዓል ዕለት “ፈጣሪያችን ሆይ አንተ ያጸደቅከው ነው አብቦ ፍሬ ያፈራው፤ ለዚህም እናመስግንሃለን በማለት እርጥብ ነገር ተይዞ ይወጣል፡፡ የተጣላ ታርቆ፣ ቂሙን ትቶ በነጻ ልቦና ፈጣሪ ንጹህ ወዳደረገው የውሃ አካል ይሄዳል። ምክንያቱም ኢሬቻ ቀልብ የሚነጻበት ቦታ ነው” ይላሉ።

ኢማና (ዶ/ር) በበኩላቸው የመስቀል ደመራ፣ ኢሬቻ እና መሰል ኃይማኖታዊና ህዝባዊ በዓላት ሰዎች ልባቸውንም ልብሳቸውንም አፅድተው በህብረት የሚያከብሯቸው በመሆኑ ንፁህ ስፍራዎችም ያስፈልጓቸዋል፡፡ የኮሪደር ልማቱ ያስገኘው አንዱ በረከትም ለእነዚህ የአደባባይ በዓላት ምቹ ማክበሪያ ቦታዎችን ነው፡፡ በመሆኑም የማህበረሰቡን ስጋና ነፍስ ለማስደሰት ትልቅ አቅምን ፈጥሯል፡፡ ይህም ለከተማዋ ተጨማሪ ድልና ውበት ነው የሚል ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ማህበረሰቡ በእነዚህ ስፍራዎች የአደባባይ በዓላትን ያለ ምንም መጨናነቅ በፍፁም ደስታና ውበት ሲያከብር ሀገራዊ ኩራት እንዲሰማው ይሆናል፡፡ የተሰራው ልማት ለእርሱ እንደሆነም በሚገባ እንዲረዳው፣ ልማቱንም እሴቱንም እንዲጠብቅና እንዲያከብር ያነሳሱታልም ብለዋል።

ወጣት ይሄነው አባተ እንደሚለው አዲሶቹ ቦታዎች ዝም ብለው የተገነቡ ሳይሆኑ  ባህላችንን የምናከብርባቸው፣ ሰዎች ተሰብስበው የሚዝናኑባቸው ናቸው፡፡ በተለይም መስቀልና ኢሬቻን የመሳሰሉ የአደባባይ በዓላት ከመንፈሳዊ አስተምህሮው ባሻገር የባህላችን ማሳያዎች ናቸው። ስለሆነም የኮሪደር ልማቱ በዓላቱን ከመቸውም ጊዜ በላቀ መልኩ እንድናከብራቸው የሚያስችለን ነው ብሏል፡፡

ኢማና (ዶ/ር) በበኩላቸው፣ ዘመናዊነት ብዙውን ጊዜ የባህላዊ ማንነት መጥፋት ስጋትን የሚያመጣ ቢሆንም በአዲስ አበባ ያለው የኮሪደር ልማት የከተማ እድገት ከባህላዊ ጥበቃ ጋር እንዴት አብሮ መኖር እንደሚችል ያሳያል። በዚህም የማህበረሰቡ ታሪካዊና ባህላዊ ቅርሶች ተጠብቀዋል። ለአብነትም የአድዋ ድል መታሰቢያ፣ የመስቀል አደባባይ እና ሌሎቹንም መጥቀስ ይቻላል፡፡ ከዚህም ባሻገር በከተማዋ የሚከናወኑ የአደባባይ በዓላት በድምቀት እንዲከበሩ ከተማዋ ያደረገችው ዝግጅት እና ልዩ ልዩ ልማት ባህልን የጠበቀ የዘመናዊ ጉዞን እየተከተለች መሆኑንም የሚያመላክት ነው፡፡ ይህ ደግሞ ከእራሱ ጋር የታረቀ፣ እሴቱንና ወጉን የጠበቀ ማህበረሰብን ለመገንባት ትልቅ ጉልበት የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

ከተማዋ ለህዝባዊ በዓላት አዲስና ደማቅ ቦታዎችን በመፍጠር መሰረተ ልማቷን ከማዘመን ባለፈ ባህላዊ ማንነቷን እያጠናከረች ትገኛለች። የከተማዋ መሠረተ ልማት ማሻሻያዎች ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ እድገቷን ከመደገፍ ባለፈ ለባህላዊ ቅርሶቿ አዲስ አድናቆት እንዲኖራት አስተዋፅኦ ያደርጋሉ። በእነዚህ በታደሱ ቦታዎች ላይ ተጨማሪ በዓላት እና ህዝባዊ ዝግጅቶች ሲካሄዱ፣ አዲስ አበባ የከተማ ልማት ከባህላዊ ጥበቃ ጋር እንዴት ሊጣጣም እንደሚችል ሞዴል ለመሆን የተዘጋጀች እንድትሆንም ያደርጋታል ሲሉ አክለዋል፡፡

በርካታ ሀገራት ጎዳናዎችን፣ አደባባዮችን እና መናፈሻዎችን ወደ ደማቅ የበዓል አከባበር ማዕከልነት በመቀየር የበለጸጉ ባህሎቻቸውን እያሳደጉ ነው ይላል  የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ተቋም (ዩኔስኮ)  በቅርቡ ይፋ ያደረገው መረጃ፡፡ ለአብነትም ጃፓን፣ ስፔን እና ዩናይትድ ስቴትስ ህዝባዊ በዓላቶቻቸው ከፍ ብለው እና ደምቀው እንዲታዩ ጎዳናዎቻቸውን እና አደባባዮቻቸውን በማስዋብ ዓለም አቀፍ ትኩረትን መሳብ ችለዋል።

ጃፓን ቶኪዮን በመሳሰሉ ከተሞቿ በየአመቱ የሚከበሩት የአደባባይ በዓላቶቿ በሰፋፊ አደባባዮች፣ መንገዶችና ፓርኮች ላይ የበዓሉ ታዳሚዎች በአበቦች፣ በዛፎች እና በውብ ፏፏቴዎች ደስ ብሏቸው እንዲያሳልፉ ታደርጋለች፡፡ ይህም በመላው ዓለም በዓላቱ ትኩረት እንዲስቡ ምክንያት እንደሆነም በመረጃው ተመላክቷል፡፡

ስፔን፣ ዩናይትድ ስቴትስ እና ቻይናን የመሳሰሉ የዓለማችን ሀገራት ለባህላዊና ኃይማኖታዊ የአደባባይ በዓላት ምቹ ሁኔታን በመፍጠር የዜጎችቸውን የሀገር ፍቅር ከፍ ከማድረጋቸውም በላይ ዓለም አቀፍ ትኩረትን በመሳብ በብዙ መልኩ ተጠቃሚ ስለመሆናቸውም የዩኔስኮ መረጃ ያመለክታል፡፡

በመለሰ ተሰጋ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review