84ኛዉ የዐርበኞች (የድል) በዐል በአዲስ አበባ አራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ሐውልት በሚገኝበት ስፍራ ተከብሯል፡፡
የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ታየ አፅቀሥላሴ አርበኛ አባቶቻችን የከፈሉት መስዋትነት ማንነቱ ያልተበረዘ ህዝብ የተከበረች እና ዳር ድንበሯ የታፈረ ሀገርን አስረክበውናል ብለዋል፡፡
ፕሬዚዳንቱ አሁን ባለው አውድ በድህነት ላይ ጦር መስበቅ አሸንፎም የበለፀገች ሀገርን እውን ማድረግ የዚህ ትውልድ የቤት ስራ ነው ብለዋል፡፡
ለድሉ መመዝገብ ህብረት እና አንድነት ትልቁን ስፍራ ይወስዳል ያሉት ፕሬዚዳንት ታየ የአሁኑ ትውልድም አብሮነት እና ህብረትን ከቀደምት አባቶቹ ሊማርም ሊወርስም ይገባል ብለዋል፡፡
የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መስፍን፣ የአርበኛ አባቶች ገድል ትውልድ ተሻጋሪ ለአሁኑ ትውልድም አስተማሪ አብሮነትን እና አሸናፊነትን ዘካሪ ነው ብለዋል፡፡
አዲስ አበባ ታሪክን ከዘመናዊነት ጋር አወዳጅታ ሰርታለች ያሉት ልጅ ዳንኤል የአራት ኪሎ የአርበኞች መታሰቢያ ዘመኑን የሚመጥን ታሪክንም ባጎላ መልኩ በመታደሱ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምስጋና ችረዋል፡፡
በተመስገን ይመር