ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ አጸፋዊ ነው የተባለለትን ባለ ሁለት አሃዝ ታሪፍ ጣለች

You are currently viewing ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ አጸፋዊ ነው የተባለለትን ባለ ሁለት አሃዝ ታሪፍ ጣለች

AMN – መጋቢት 27/2017 ዓ.ም

ቻይና ከአሜሪካ ወደ ሀገሯ በሚገቡ ምርቶች ላይ አጸፋዊ ነው የተባለለትን ባለ ሁለት አሃዝ ታሪፍ መጣሏን አስታወቀች፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከትላንት ወዲያ መላውን አለም ያዳረሰ ታሪፍ ከጣሉ በኋላ ቻይና የመጀመሪያ ነው የተባለለትን ታሪፍ መጣሏን ገልጻለች፡፡

ዓለም አቀፍ አክሲዮኖች እያሽቆለቆሉ በመምጣታቸዉ ቻይና በአሜሪካ ምርቶች ላይ የ34 በመቶ ታሪፍ በመጣል ለትራምፕ ምላሽ የሰጠች የመጀመሪያዋ ሀገር ሆናለች።

ቻይና ከፈረንጆቹ ሚያዝያ 10 ጀምሮ ወደ ሀገሯ በሚገቡ በሁሉም የአሜሪካ ምርቶች ምርቶች ላይ የ34 በመቶ ቀረጥ እንደምትጥል አርብ ዕለት ማስታወቋ ይታወሳል።

ይህም የአሜሪካን ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አዲስ ታሪፍ ማውጣታቸውን ተከትሎ እየተወሰዱ ያሉ የመከላከያ እርምጃዎች አካል ነው ስትል ቻይና ገልጻለች።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ ዓለም አቀፍ አክሲዮኖች ለሁለተኛ ቀን መቀነሳቸውን የፍራንስ 24 TV ዘገባ ያመለክታል።

በወርቅነህ አቢዮ

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review