AMN – ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም
ኅብረተሰቡ ሀገርን አረንጓዴ በማልበስ የትውልድ ኃላፊነቱን እንዲወጣ የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ ጥሪ አቀረቡ።
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮና በሁሉም ክፍለ ከተሞች የሚገኙ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች እንዲሁም በዘርፉ የተሰማሩ አካላት የችግኝ ተከላ መርሐ-ግብር አካሂደዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ 40 ሺህ ችግኞችን ለመትከል እቅድ ይዞ ወደ ተግባር ገብቷል ያሉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ኃላፊ አቶ ጃንጥራር ዓባይ በዚህም በርካቶች ተሳትፎ እያደረጉ ነዉ ብለዋል።
ኅብረተሰቡ ችግኝ በመትከል እያሳየ ያለውን ርብርብ በመንከባከብ እና ሀገርን አረንጓዴ በማልበስ የትውልድ ኃላፊነቱን እንደወጣ ጥሪ አቅርበዋል።
ከኢንዱስትሪዎች የሚወጣ በካይ ጋዝን በመቋቋም ጤናማ ትውልድ እንደፈጠርና የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመከላከል ሁሉም ተሳትፎውን እንዲያጠናክርም ምክትል ከንቲባው ጠይቀዋል፡፡
“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሣብ እየተከናወነ በሚገኘው 6ኛው ዙር የአረንጔዴ አሻራ መርሃ-ግብር የአዲስ አበባ ከተማ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ በየደረጃው ያሉ አመራርና ሠራተኞች በተገኙበት ነዉ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ በለሚ ኢንዱስሪ ፓርክ የተካሄደው::
በአንዋር አህመድ
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!