ነዋሪዎቻችንን ካረጀ እና ለመኖር ምቹ ካልሆነ የካዛንቺስ አካባቢ እንዲወጡ አድርገን ለኑሮ ምቹ የሆነ ቤት እና አካባቢ እንዲገቡ በማድረግ የሰው ህይወትን የመቀየር ስራ ሰርተናል ፡-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

AMN ኅዳር -30/2017 ዓ.ም

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ነዋሪዎቻችንን ካረጀ እና ለመኖር ምቹ ካልሆነ የካዛንቺስ አካባቢ እንዲወጡ አድርገን ለኑሮ ምቹ የሆነ ቤት እና አካባቢ እንዲገቡ ያደረግን ሲሆን በዚህም የሰው ህይወትን የመቀየር ስራን ሰርተናል ብለዋል።

ዛሬ የገላን ጉራ የመኖሪያ እና የተቀናጀ የልማት መንደርን መርቀን ከካዛንቺስ በልማት ለተነሱ ነዋሪዎቻችን አስረክበናል።

የኢትዮጵያ መልክ የሆነችው አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ አበባ ለማድረግ በገባነው ቃል መሰረት፣ መሰረተ ልማት ከማሟላት በተጨማሪ የሰው ህይወትን ለማሻሻል እና የነዋሪዎቻችንን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ትልቅ ትኩረት ሰጥተን በመስራት ላይ እንገኛለንም ነው ያሉት ከንቲባዋ።

ከንቲባዋ አያይዘውም ነዋሪዎቻችንን ካረጀ እና ለመኖር ምቹ ካልሆነ የካዛንቺስ አካባቢ እንዲወጡ አድርገን ለኑሮ ምቹ የሆነ ቤት እና አካባቢ እንዲገቡ ያደረግን ሲሆን በዚህም የሰው ህይወትን የመቀየር ስራን ሰርተናል።

ከካዛንቺስ አካባቢ ለልማት በፈቃደኝነት የተነሳችሁ እና ከጎናችን የቆማችሁ ነዋሪዎችን ስለ ትዕግስታችሁ እና ድጋፋችሁ እያመሰገንኩ፣ ይህ ስራ እንዲሳካ ህግ እና አሰራሩን በመቀበል ቦታውን በፈቃደኝነት ለልማት የለቀቃችሁ የአካባቢው አርሶ አደሮችንም ላመሰግናቸው እወዳለሁ ብለዋል።

ይህን ታላቅ ስራ በአጭር ጊዜ ውስጥ ገንብታችሁ ያጠናቀቃችሁ ኮንትራክተሮችን፣ አማካሪ ድርጅቶችን፣ ድጋፍ ያደረጋችሁ አካላትን፣ ያስተባበራችሁ አመራሮችን እንዲሁም የክፍለከተማው አመራሮችን በራሴ እና በከተማ አስተዳደራችን ስም ላመሰግናችሁ እወዳለሁ ብለዋል ከንቲባዋ በመልእክታቸው።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review