አሜሪካ ውስጥ 250 ሚሊየን የሚደርስ የንብ መንጋ የደኅንነት ስጋት መፍጠሩ ታውቋል፡፡
የንብ መንጋው በሀገሪቱ ዋና ከተማ ዋሺንግተን የንብ ቀፎዎቸን ጭኖ ሲጓዝ የመገልበጥ አደጋ ካጋጠመው የጭነት መኪና ያፈተለከ ነው፡፡
የከተማዋ ባለስልጣናት ህዝቡ ራሱን ከንብ መንጋ ንድፊያ እንዲጠብቅ አስጠንቅቀዋል፡፡
የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች ከበርካታ የንብ ተቆጣጣሪ ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት፣ ንቦቹን ወደ ቀፏቸው ለመመለስ ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኙ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡
አደጋው የደረሰባት የዋትኮም አውራጃ የፖሊስ ኃላፊዎች፣ ከ31 ሺህ ኪሎ ግራም በላይ ክብደት ያላቸው ንቦቹ ወደ ቀፏቸው እስኪመለሱ ድረስ አካባቢው ለመንገደኞች ዝግ እንደሚሆን አስታውቀዋል፡፡
ንግስት ንቦቹን ወደ ቀፏቸው በመመለስ መንጋውን ለመቆጣጠር የሚደረገው ጥረትም እስከ ሁለት ቀናት ድረስ ሊወስድ እንደሚችልም አመላክተዋል፡፡
በኢዮብ መንግስቱ