አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከሚገኙት የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ

You are currently viewing አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከሚገኙት የፈረንሳይ እና የእንግሊዝ ኤምባሲ ኃላፊዎች ጋር ተወያዩ
  • Post category:ዓለም

AMN-ሰኔ 03/2016 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ፣ በኢትዮጵያ የፈረንሳይ አምባሳደር ሬሜ ማሪሾንና የእንግሊዝ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ አንድሪው ኦኬንደንን ዛሬ በጽህፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

አምባሳደር ምስጋኑ ከፈረንሳዩ አምባሳደር ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ኢትዮጵያ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነትን በተሟላ መልኩ ተግባራዊ ለማድረግ ያላትን ቁርጠኝነት አብራርተው ለአፈፃፀሙ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ድጋፍ እንደሚቀጥል ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ሁለቱ ወገኖች በቀጣናዊ የጋራ ጉዳዮች በተለይም የቀጣናውን ሰላምና መረጋጋት ለማረጋገጥ ተባብሮ የመሥራት አስፈላጊነት ላይ ተወያይተዋል።

በተመሳሳይ አምባሳደር ምስጋኑ ከእንግሊዝ ኤምባሲ ጉዳይ ፈፃሚ ጋር ባደረጉት ውይይት ደግሞ፣ እንግሊዝ ለአዲስ አበባ ከተማ ኮሪደር ልማት ፕሮጀክት የምታደርገውን ድጋፍ አድንቀዋል።

ጉዳይ ፈፃሚው በበኩላቸው በኮሪደር ልማት ፕሮጀክቱ ያዩትን ለውጥ አድንቀዋል።

ሁለቱ ወገኖች በጋራ የሁለትዮሽና ክልላዊ ጉዳዮች ላይም መወያየታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

Addisababa

#Ethiopia

ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!

https://linktr.ee/AddisMediaNetwork

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review