አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከቻይናው አምባሳደር ቼን ሀይ ጋር ተወያዩ

You are currently viewing አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከቻይናው አምባሳደር ቼን ሀይ ጋር ተወያዩ

AMN- መስከረም 28/2017 ዓ.ም

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ምስጋኑ አርጋ በኢትዮጵያ ከቻይና አምባሳደር ቼን ሀይ ጋር በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።

በውይይታቸውም በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን ዘርፈ ብዙ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል።

ሁለቱ ወገኖች በብሪክስ እና በሌሎች ዘርፈ ብዙ ትብብሮች ዙሪያ ግንኙነቶችን ማሻሻል በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ሀሳቦችን መለዋወጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

0 Reviews ( 0 out of 0 )

Write a Review