AMN- ሰኔ 4/2016 ዓ.ም
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከሩሲያ አቻቸው ሰርጌይ ላቭሮቭ ጋር ከብሪክስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ጎን ለጎን ተወያይተዋል።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በብሪክስ ማዕቀፍ ስር ትብብራቸውን ማጠናከር በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ተወያይተዋል።
ሚኒስትሮቹ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ታሪካዊ የሁለትዮሽ ግንኙነት የበለጠ ለማስፋት ያላቸውን ቁርጠኝነትም ማረጋገጣቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።
ትክክለኛውን የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዲጂታል ሚዲያ የትስስር አውታሮችን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን!